Connect with us

ጀነራሉ የሚቆጫቸው አማርኛ መማራቸው ነው

ጀነራሉ የሚቆጫቸው አማርኛ መማራቸው ነው
Photo: Social media

ፓለቲካ

ጀነራሉ የሚቆጫቸው አማርኛ መማራቸው ነው

ጀነራሉ የሚቆጫቸው አማርኛ መማራቸው ነው፤ እኔን ግን የሚቆጨኝ አማርኛ ብቻ መቻሌና ትግርኛ አለመማሬ ነው፡፡
(ከስናፍቅሽ አዲስ)

አንድ ስማቸው ብዙም የማይጠቅመን ጄነራል በትግራይ ሚዲያ ሀውስ ላይ ቀርበው አማርኛ መማራቸው እንደሚቆጫቸው ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩ የግል ምርጫቸው ቢሆንም ሌላ ቋንቋ ጠልቶ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ሠራዊትን ለመምራት ማሰብ አማርኛ መማርን ከመጥላት በፊት ሊጠላ የሚገባው ሀሳብ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ቋንቋን ብሔር ሰጥቶ ማሰብ ቀውሱ ፌዴራሊዝም የጣለብን መከራ ነው፡፡ ቋንቋ መገልገያ መሳሪያ ነው፡፡ ማንነት ነው የሚለው ስለጎላ መገልገያ መኾኑን ተረስቶ ተጨማሪ ቋንቋ መቻል የሌላን ማንነት መቀበል አድርጎ መውሰድ ወረርሺኝ ሆነ፡፡

አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚበዙበት መጪው ግዜ ምነው ሌላ ቋንቋ በቻልኩ የሚያስብል የውድድር ዘመን ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው ጄነራሉ ተጨማሪ ቋንቋ መማራቸውን በተማሩት ተጨማሪ ቋንቋ ይቆጨኛል ያሉት፡፡

እኔ አማርኛ ተናጋሪ ስለሆንኩ የሚቆጨኝ ትግርኛ ባለመቻሌ ነው፡፡ ትግርኛ ተጨማሪ ቋንቋ ስለሆነ ያስፈልገኛል፡፡ ቋንቋ መቻል የቋንቋውን ባለቤት ማፍቀር ወይም በቋንቋው ባለቤት ቅኝ መገዛት አይደለም፡፡ እንዲያ ቢሆን እንግሊዘኛ መናገርን የእውቀት ጥግ አድርገንው ባላወራን፤ እንግሊዘኛ መናገር የእውቀት ጥግ የሆነበት ምክንያት በዚህ ተጨማሪ ቋንቋ አለም ገበያ ውስጥ መግባት ያስችላል፡፡

አማርኛ በኢትዮጵያ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፡፡ አማርኛን መቀነስ ሳይሆን ተጨማሪ ቋንቋን መጨመር የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ ነግዶ ለማትረፍም በሉት ቤተ መንግስት ገብቶ ሀገር ለመምራት ዛሬ ሁለት ሦስት ቋንቋ ማወቅ የሚያስቆጭ ሳይሆን የሚያስቀድም ነው፡፡

ጀነራሉ ላይ የተፈጠረው ቁጭት የብዙ ሰዎች ቁጭት አይመስለኝም፤ መማሬ ይቆጨኛል የሚል ሰው ትንሽ ነው፡፡ አለመማሩ የሚቆጨው ይበልጣል ለዚህ ነው ተጨማሪ ቋንቋ ማወቅ ተጨማሪ ጥቅም የሚሆነው፡፡ እናም አማርኛ በመማርዎት የቆጨዎትን ያህል ትግርኛን በተጨማሪ ቋንቋነት አለመማሬ ደግሞ እኔን ይቆጨናል፡፡ ብማረው ኖሮ እንዴት ያለሽ ልጃችን ነሽ የሚሉኝ እርስዎ ነበሩና፤

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top