Connect with us

ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ሰሜን መዘጋጃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ከህዝብ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ 19 )ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሎም ጉዳቱን ለመቀነስ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተከለከሉ ተግባራት መካከል በማንኛውም ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም አገልግሎት መስጠት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ክልከላዎቹ ሲጣሱ ይስተውላል፡፡

ሚያዝያ 18 እና 19 ቀን 2012 ዓ/ም በተለያዩ ሰዓታት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙት ራሄል ሆቴል ውስጥ 35 ሰዎች እንዲሁም ቲሊሊ በሚባል ሆቴል ውስጥ 81 ግለሰቦች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ኮማንደር ጃፋር ኸሊል ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ በዚህ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ስምንት ሰዎችን በአንድ አነስተኛ ጠባብ ቤት ውስጥ ጫት ሲያስቅም የተገኘ ግለሰብም በቁጥጥር ስር መዋሉን ክ/ከተማው አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ሃላፊ ወ/ሮ ሠጂዳ ሙስማ ገልፀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌዎችን ለማስተግበር ከፖሊስ ጋር በጋራ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቁመው በየዕለቱ ህ/ሰቡ ለሚሰጣቸው መረጃ አመስግነዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ድንጋጌን በሚጥሱ ግለሰቦች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በተመለከተ ኮማንደር ጃፋር በሰጡን አስተያየት በህጉ አግባብ አስፈላጊ መረጃዎች መሰብሰባቸውን ገልፀው የምርመራ መዝገቡን አደራጅቶ በሚመለከተው የፍትህ አካል ክስ እንደተመሰረተባቸው አብራርተዋል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን፣ እርምጃዎችን፣ የተሰጠ መመሪያን፣ ትዕዛዝን የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከ 1 ሺ እስከ 2 መቶ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚቀጣ በህጉ ተደንግጓል፡፡

via Addis Ababa Police Commision

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top