Connect with us

ከ460 ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ያለአግባብ አጥረው የተገኙ ግለሰቦችን ጉዳይ እየተጣራ ነው

ከ460 ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ያለአግባብ አጥረው የተገኙ ግለሰቦችን ጉዳይ እየተጣራ ነው
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ከ460 ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ያለአግባብ አጥረው የተገኙ ግለሰቦችን ጉዳይ እየተጣራ ነው

ከ460 ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ያለአግባብ አጥረው የተገኙ ግለሰቦችን ጉዳይ እየተጣራ ነው
* አንድ ግለሰብ ብቻ በህገ-ወጥ መንገድ 60 ሚሊዮን ብር ሰብስቧል

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ460 ሺ ካሬ ሜትር በላይ የመንግስትና የህዝብን መሬት ያለአግባብ አጥረው የተገኙ ግለሰቦችን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ አንደኛው ግለሰብ ብቻ በህገ-ወጥ መንገድ 60 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን በምርመራ ተረጋግጧል ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ መስታዎት ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ የአርሶ አደሮችን ፣ ለተቋማት ተከልለው የተቀመጡ እና በመሬት ባንክ የሚገኙ በጥቅሉ 460 ሺ ካሬ ሜትር ወይም 46 ሄክታር መሬት በህገ-ወጥ መንገድ አጥሮ ማስቀመጡን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ግርማ ተሰማ ገልፀዋል፡፡

በወንጀሉ የተጠረጠረው ግለሰብ መሬቱን አጥሮ ከማስቀመጡ ባሻገር አርሶ አደሮችን የአክሲዮን ተጠቃሚ ትሆናላችሁ በማለት እንዲሁም በውጪ ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጰያውያን በሪል ስቴት ስም መኖሪያ ቤት እገነባለሁ ብሎ 60 ሚሊዮን ብር ሰብስቧል፡፡
ተጠርጣሪው ግለሰብ በአሁኑ ወቅት በፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት በእስር ላይ እንደሚገኝና የህግ አግባብ በመከተል በፍርድ ቤት ንብረቶቹ መታገዳቸውን ኮማንደር ግርማ ተናግረዋል፡፡

የክፍለ ከተማው አስተዳደር የአቃቤ ህግ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ በበኩላቸው ግለሰቡ ከአዲስ አበባ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በማታለል በያዘው አራት መቶ ስልሳ ሺ ካሬ ሜትር(46 ሄክታር) ቦታ ላይ ግንባታ ሲያከናውንና መሬቱን ሸንሽኖ ሲያከራይ ተገኝቶ ከህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲታቀብ ቢገለፅለትም ፈቃደኛ እንደልሆነ ገፀዋል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ጀሞ እና አካባቢው አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዳነ ፊጣ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ግለሰብ በአርሶ አደሮቹ ስም በመነገድ የመንግስትና የህዝብ የሆነውን መሬት በህገ-ወጥ መንገድ ሲጠቀም ቆይቷል፡፡ ግለሰቡ መሬቱን መጠቀም የሚያስችል ምንም ዓይነት ሰነድ እንደሌለው አስረድተዋል፡፡

መንግስት ከሚከፍላችሁ የተሻለ ካሳ እከፍላችኋለሁ ፤ መሬቱን አልምተን ጥሩ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ወዘተ በማለት መሬቱን አጥሮ በማስቀመጡ ከመሬቱ ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም ሳያገኙ መቅረታቸውን የአካባቢው አርሶ አደሮች አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ሌላኛው ግለሰብ ከክፍለ ከተማው መሬት ማኔጅመንት ከአንዳንድ ሰራተኞች እና ኃላፊነት ከማይሰማቸው ደላሎች ጋር በመመሳጠር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 1 ፣ 11 እና 12 እያንዳንዳቸው 500 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው የ15 ቦታዎችን ሀሰተኛ የመሬት ባለቤት ማረጋጋጫ ካርታ በማዘጋጀት 7ሺ 500 ካሬ ሜትር በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ግሉ ማዞሩን በምርመራ እንደተረጋገጠና ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ በህገ-ወጥ መንገድ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ሰነዶች በኤግዚቢትነት መያዛቸውን ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም ከእነዚህ ህገወጦች ጋር በመመሳጠር በሀሰተኛ ሰነድ ላይ ተመስርተው ህጋዊ እንዲመስሉ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እስከ መስጠት የደረሱ 3 የክፍለ ከተማው የመሬት ማኔጅመንት ሰራተኞችና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ደላሎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ወንጀሉን እያጣራ መሆኑን ኮማንደር ግርማ ገልፀው ምርመራውን በማስፋት በዚህ ህገ- ወጥ ድርጊት ላይ ተሳትፎ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች ሆኑ ሌሎች ግለሰቦችን ህግ ፊት ለማቅረብ ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉንና በዚህ ወንጀል ምክንያት መንግስት ከ22.3 ሚሊዮን ብር በላይ ማጣቱን ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡ #ኢፕድ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top