Connect with us

አየር መንገዱ የኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ

Photo: Social media

አለም አቀፍ

አየር መንገዱ የኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ

አየር መንገዱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው ጥረት ላይ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታወቁ ።

ዋና ስራ አስፈጻሚውን አቶ ተወልደ ገብረማርያምን ጠቅሶ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት አድን የህክምና አቅርቦትን ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማጓጓዝ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው ጥረት ላይ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው “በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዘመናዊው የኢትዮጵያ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት የፋርማሲ ክንፍ እንዲሁም የጭነትና የተሳፋሪዎችን አገልግሎት በመስጠት አለምን እያገለገልን በመሆኑ ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።

“አዲስ አበባ የሰብአዊነት አየር ማዕከል ተብላ በዓለም የምግብ ፕሮግራምና በአለም ጤና ድርጅት ተሰይማለች” ያሉት አቶ ተወልደ፤ ”በምንሰጠው የላቀ አገልግሎትና ባለን 127 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችና ሰፊ የአገልግሎት መረብ በአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ጭነት አገልግሎት አቅራቢ ለመሆን የበለጠ ጠንክረን እንሰራለን” ብለዋል።

አሁን ላይ የኢትዮጵያ የጭነትና የሎጅስቲክ አገልግሎት በወር በአማካይ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኪሎግራም

የህክምና፣ የባዮሎጂካል፣ ባዮቴክኖሎጂ፣ የክትባትና የመሳሰሉት የጤና ምርቶች እያጓጓዘ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ኤጀንሲዎች፣ ለጋሽ አገሮችና በጎ አድራጊዎች የህክምና ቁሳቁሶችን በአፍሪካ ለማከፋፈል አዲስ አበባን ማዕከል አድርገው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።

መግለጫው በአፍሪካ በትልቁ የትራንስፖርት ጭነት ተርሚናል ስር ያለው ዘመናዊው የኢትዮጵያ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት የፋርማሲ ክንፍ በአፍሪካና በሌሎች አገሮች የህክምና ቁሳቁሶች መላኪያ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ መሆኑን አመልክቷል።

የፋርማሲ ክንፉ ባለው የሙቀት መቆጣጠሪያ ስርዓት በተለያዩ የሙቀት ክልሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ለመያዝ የሚያስችል መሆኑን አብራርቷል።

አየር መንገዱ የተለዩና የሰለጠኑ ባለሙያዎች በዓለም አየር መንገድ ትራንስፖርት ማህበር ህግና መመሪያዎች እንዲሁም ሌሎች በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ባሉ ተቆጣጣሪ አካላት አሰራር መሰረት ስራውን እያከናወነ ነውም ብሏል።

አዲስ ዘመን ሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓም

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top