Connect with us

በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮሮናን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮሮናን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ
Photo Facebook

ዜና

በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮሮናን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮሮናን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

ኬንያ ውስጥ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር በላይ (1,594,558.00 ብር) ያህል በኢትዮጵያ ኮሮናን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መድረክ (ፔፕሶድ)፣ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የንግድ ባንክ አባላት (ቲ.ዲ.ቢ) ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በንግድና በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን “ወገኖቻችንን እንታደግ” በሚል ባደረጉት እንቅስቃሴ የሰበሰቡትን 1,594,558.00 ብር በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን ለአምባሳደር መለስ ዓለም ሚያዚያ 15 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም አስረክበዋል፡፡

የኢትዮጵያውያኑን ድጋፍ ከተቀበሉ በኋላ አምባሳደር መለስ ባደረጉት ንግግር ኬንያ የሚገትኙ ወገኖቻችን ለአገራቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው የሚውለውን ድጋፍ በማሰባሰባችሁ የሞራል እና የዜግነት ግዴታችሁን ስለተወጣችሁ እፎይታ ሊሰማችሁ፤ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል።

ዜጎች በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ ለወገኖቻቸው ካልደረሱ መቼ አለን ሊሉ ይችላሉ ያሉት አምባሳደር መለስ፣ ሌሎች በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በቀጣይ በሚኖሩ ተመሳሳይ ፕሮግራሞች የድጋፍ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ኬንያ ውስጥ ለችግር የተዳረጉ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባ የጠቀሱት አምባሳደር መለስ ፤ ከኬንያውያንም በክፉ የሚደርሱልን ህዝቦች ናቸውና አጋርነታችንን ማሳየት ይገባናል ብለዋል።

በኬንያ በተመድ ጽ/ቤት የሚሰሩ የኢትዮጵያውያንን በመወከል ከአባላቱ የተሰበሰበውን ገንዘብ ያስረከቡት ዶ/ር አስፋው ኩምሳ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የኮሮና ወረርሽን የመከላከል ጥረት በመደገፋቸው ታላቅ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀው በቀጣይነት ለመደገፍም ቃል መግባታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። # ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top