Connect with us

የካ ኮተቤ ሆስፒታል ግላብ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ

የካ ኮተቤ ሆስፒታል ግላብ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የካ ኮተቤ ሆስፒታል ግላብ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ

የካ ኮተቤ ሆስፒታል ግላብ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተጠቁ ሰዎች ህክምና ከሚያገኙበት ኮተቤ የካ ሆስፒታል ግላብ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ወረርሽን ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር መንግስትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ህበረተሰቡን በማስተባበር በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል በልዩ ሁኔታ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ህክምና የሚከታተሉበት የህክምና ማዕከል ነው፡፡

መንግስት እና ዜጎች ቫይረሱን ለመከካከል ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ባሉለበት በአሁኑ ወቅት የሆስፒታሉ ሁለት የቧንቧ ሰራተኞች ከሌሎች ሁለት ግበረአበሮቻቸው ጋር በመሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 17 ከሚገኘው ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የሰሌዳ ቁጥር A 74615 አ/አ ቶዮታ የቤት መኪና ግምቱ ከ3ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ግላብ ሰርቀው በጥበቃ ሰራተኞችና በፖሊስ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ የኮቶቤና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ ገልፀዋል፡፡

ግለሰቦቹ ወንጀሉን መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ እንደፈፀሙ የጣቢያው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፀጋዬ ጴጥሮስ ተናገረው ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚረዳ ምርመራ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለና በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በእስርላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል አስተዳደሪ አቶ ዳዊት ሲሳይ በበኩላቸው ቫይረሱ ከተከሰተበት ዕለት አንስቶ መላው የሆስፒታሉ ሰራተኞች ሙያዊ ብሎም ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ኃላፊነታቸውንእየተወጡ ባለበት ሆኔታ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ስራቸውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል ውስጥ መግባታቸው አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡ ሆስፒታሉ እና ፖሊስ ያላቸው ትሰስር ጠንካራ በመሆኑ ተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ መያዝ እንደተቻለ ኃላፊው ጨምረው ገልፀው ወደፊትም ያላቸውን የስራ ግንኙነት በማጠናከር እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

ምንጭ:- ኢፕድ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top