Connect with us

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ክልከላዎች ተፈጻሚ አለመሆን ፖሊስን አሳስቧል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ክልከላዎች ተፈጻሚ አለመሆን ፖሊስን አሳስቧል
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ክልከላዎች ተፈጻሚ አለመሆን ፖሊስን አሳስቧል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ክልከላዎች ተፈጻሚ አለመሆን ፖሊስን አሳስቧል

በሀገራችን ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ መንግስት እና ማህበረሰቡ ተቀራርበው በመስራታቸው ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም መስተካከል ያልቻሉ ጉዳዮችን በምልከታ፣ በክትትል እና ቁጥጥር ለማረጋገጥ እንደተሞከረው ርቀትን ያለመጠበቅ ችግር አሁንም እየተስተዋለ መሆኑን ክቡር ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ባደረገው የቁጥጥር ስራ ለቫይረሱ በሚያጋልጥ መልኩ አሳቻ ቦታ ላይ ተሰብስበው ካርታ፣ ከረንቡላ፣ ቴኒስ እና የመሳሰሉት ጨዋታዎችን የሚጫወቱና ህገ ወጥ ተግባራት እንዲፈጸም ከለላ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦችም ታይተው ህጋዊ እርምጃም ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡

በአንዳንድ መጠጥ ቤቶች ሰዎች በመሰባሰብ ለቫይረሱ በሚያጋልጥ መንገድ የሚዝናኑ መኖራቸው፣ በገበያ ቦታዎች መለስተኛ መስተካከል የሚስተዋል ቢሆንም አሁንም በርካታዎቹ የተሰጠውን መመሪያ እና ማሳሰቢያ ወደ ጎን በመተው ከተለመደው የገበያ ስርዓት ባልተለየ መልኩ እየተገበያዩ ስላሉ በፍጥነት ካላረምነው የተጋላጭነት መጠናችን ሊጨምር ይችላል ያሉት ኮሚሽነር ጄነራሉ በሀገሪቱ በቂ አቅርቦት እያለ በመደበቅ በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የጅምላም ሆነ የችርቻሮ ነጋዴዎች ላይ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ ተናግረዋል፡፡

የአሽከርካሪዎች የሌሊት ጉዞ ማድረግ፣ ከተፈቀደው የሰው ብዛት በላይ ጭኖ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አሁንም አለመስተካከሉና ከታሪፍ ውጭ የሚያስከፍሉና ከሚገባቸው ከ50 በመቶ በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይም አዋጁ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ኮሚሽነር ጄነራሉ በመግለጫው ዝውውር እንዲደረግባቸው ከተለዩ ድንበሮችና ኬላዎች ውጪ በሌሎች መግቢያና መውጫዎች ተገቢውን የፖሊስ ሃይል በመመደብ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ፣ የፌደራል፣ የክልል ፖሊስ እና ሌሎች ልዩ ልዩ የጸጥታ አካላት በአንድ የግብረ ሃይል አሰራር ውስጥ በመግባት በቅንጅት ህጉን እንደሚያስከብሩም አንስተዋል፡፡

በየእለቱ የሀገሪቱ መንግስት፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የአለም ጤና ድርጅት እና ሚዲያዎች የሚሰጡትን መረጃ እና መመሪያዎችን በአግባቡ መከታተል እና ተግባራዊ ማድረግ ምርጫ የሌለው የወቅቱ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

(የፌ/ፖሊስ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top