Connect with us

በክፉ ጊዜ እንራራቅ በመልካም ጊዜን እንድንደሰት – የኪኒ ጥበብ ባለሙያዎች ጥሪ

በክፉ ጊዜ እንራራቅ በመልካም ጊዜን እንድንደሰት – የኪኒ ጥበብ ባለሙያዎች ጥሪ
Photo: Social media

ጥበብና ባህል

በክፉ ጊዜ እንራራቅ በመልካም ጊዜን እንድንደሰት – የኪኒ ጥበብ ባለሙያዎች ጥሪ

ኪነ ጥበብን ለህብረተሰባዊ ንቅናቄ ለመጠቀም አንደኛው የጥበብ ፍልስፍና መንገድ ሲሆን በተለይ በስልጣኔ ወደኋላ የቀረ ማህበረሰብን ወደተሻለ ደረጃ ለማሻገር ኪነ ጥበብን መጠቀም አንዱ ስልት ነው።

በዚህም በተለያየ የኪነ ጥበብ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ከያኒያን በአሁኑ ወቅት ዓለምን እያስጨነቀ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማህበረሰቡን ለማንቃትና ለማስገንዘብ ይጥራሉ።

የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉም፤ ከቫይረሱ ለመከላከል የሚሰጡ መመሪያዎችን ህብረተሰቡ ተግባራዊ እያደረገ እንዳልሆነ ትዕዝብቱን ጠቅሶ ‘እባካችሁ’ ሲል ይጣራል።

ከሰሞኑም ከትንሳዔ በዓል ጋር ተያይዞ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በግብይት ሰፍራዎች፣ በመኖሪያ አካባቢዎች በጥንቃቄ በመተሳሰብ እንዲያከናውኑ፣ ለበዓል ፍጆታ ምርት የሚያቀረቡ ነጋዴዎችም አዳዲስ ስልቶችን በመፍጠር ለሸማቹ እንዲደርሱ ይጠይቃል።

ሌላው ዕውቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አርቲስት ንብረት ገላው ”ወቅቱ እውቅና የሰጠንን ህዝብ የምናገለግልበት ጊዜ ነው” ይላል።

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በመዘዋወር የቅስቀሳ ስራ ሲሰራ የነበረው አርቲስቱ፤ በዓለም ላይ ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና አሁንም በመዛመት ላይ ስላለው ቫይረስ አስቸጋሪነት ይናገራል።

ሁሉም ታዋቂ ሰዎችም ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ህዝቡ ከአደገኛው ወረረሽኝ ራሱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸውም ይገልጻል።

ሌሎች ለኢዜአ አስተያይታቸውን የተናገሩት አንጋፋ ድምጻዊያን ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) እና አረጋኸኝ ወራሽም የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ስላለው ወረርሽኝ የ’እንጠንቀቅ’ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ህብረተሰቡም በንግድ ቦታዎችም ሆነ በየቤቱ በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን እንዲተገብር አርቲስቶቹ ጥሪ አቅርበዋል።

‘ክፉውን ጊዜ በመራራቅ፤ ማህበራዊ ግንኙነታችንን በመገደብ በመልካም ጊዜ እንደሰት’ መልክዕታቸው ነው።

#ኢዜአ

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top