Connect with us

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
Photo Facebook

ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 10 ደርሷል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች መካከል አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ክትትል እያደረጉ ከሚገኙት መካከል 10 ግለሰቦች አገግመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለሶስት ሺህ 500 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው አራቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንም ነው የገለጹት።

ሁለቱ ወንድ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ከእነዚህም መካከል አንድ የ30 ዓመት ሴትና አንድ የ29 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

አንድ የ33 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ደግሞ የአሜሪካ አገር የጉዞ ታሪክ ያላት ናት።

ሌላኛው ግለሰብ የ42 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ ሲሆን፤ ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው መሆኑና በህመሙ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ክትትል እያደረጉ ከሚገኙ ግለሰቦች መካከል ተጨማሪ ስድስት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ይፋ አድርገዋል።

ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።

በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ሲያደርጉ የነበሩት የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊት ትናንት ህይወታቸው ማለፉን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል የሚደረግላቸው ህሙማን አለመኖራቸውን አስታውቀዋል።

#ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top