Connect with us

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ተገኘበት

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ተገኘበት

ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ተገኘበት

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 294 ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ የተገኘበት መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለበት የተረጋገጠበት ግለሰብ የካናዳ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው።

ግለሰቡ ከካናዳ ወደ ዱባይ ከዛም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደነበርም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ህብረተሰቡ በንቃት ገቢራዊ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 48ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው የተሸኙ ሲሆን ቀሪ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።

#ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top