Connect with us

የኮሮና ወርሽኝ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከ300 በላይ ቤቶችን የገነቡ ተያዙ

የኮሮና ወርሽኝ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከ300 በላይ ቤቶችን የገነቡ ተያዙ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የኮሮና ወርሽኝ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከ300 በላይ ቤቶችን የገነቡ ተያዙ

በአዲስ አበባ ከተማ የወንጀል ድርጊቶቹን ለመግታት ህብረተሰቡን በማወያየት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በተደረገዉ ዘመቻ ቀደም ሲል የተሰረቁ 14 ላፕቶፖች፣ 567 የሚደርሱ ተንቀሳቃሽ ስልኮች እና 14 ታብሌቶች መያዛቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አድማሱ ኢፋ ገለጹ፡፡

በዚህ ሳምንት ብቻ ከስርቆቱ ጋር ግንኙነት ያላቸዉ 20 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በህጋዊ መንገድ እንዲጠየቁ የምርመራ መዝገብ እየተደራጀባቸዉ መሆኑንም ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ ሁኔታን እንደ ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመው ለመበልጸግ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸውን የገለጹት ኮማንደር አድማሱ የፍጆታ እቃዎችን በመደበቅ በአቋራጭ ለመበልጸግ ሙከራ ያደረጉ 4 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል፡፡

የፖሊስ አባላቱን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመከላከል ስራ ላይ መጠመድ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በቡልቡላ (ወረዳ 14 አካባቢ) የመሬት ወረራን በማካሄድ ከ300 በላይ የሚሆኑ ህገ ወጥ ቤቶችን ሲገነቡ የነበሩ ግለሰቦችንም ፖሊስ በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን መምሪያ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በቡድን በመደራጀት የቤቶች ልማት ንብረትን የዘረፉና ሙከራ ያደረጉ 20 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠሉንም ኮማንደሩ ጠቁመዉ ንብረቶቹን ሲጭኑባቸዉ የነበሩ ተሽከርካሪዎችም መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተሰጠዉን መመሪያ አብዛኛዉ የማህበረሰብ ክፍል ተቀብሎ ተግባራዊ ያደረገ ቢሆንም አሁንም ግን ገንዘብ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ አንዳንድ ጫት ቤቶች፣ ሺሻ ቤቶ እና የሌሊት ጭፈራ ቤቶች በመኖራቸዉ ፖሊስ የጀመረዉን እርምጃ የመዉሰድ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

ለሀገር፣ ለወገን የሚያስቡ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ከሰዉኛ አስተሳሰብ ወጣ ባለ መንገድ ህገ ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት አሉና ህብረተሰቡ በማዉገዝ ለህግ አስከባሪዎች የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ኃላፊዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝን የምንከላከልበት ወቅት ነዉና መፈጸም አለበት ብሎ ህግ የሚፈቅደው የወንጀል አይነት ባለ መኖሩ ማንኛውንም ህገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ከተግባራቸዉ ሊቆጠቡ እንደሚገባም የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዉ አሳስበዋል፡፡(ምንጭ፡-የፌ/ፖሊስ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top