Connect with us

“የህፃናት የኖቭል ኮሮና ህመም” – ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም

"የህፃናት የኖቬል ኮሮና ህመም" - ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም
Photo: Social media

ጤና

“የህፃናት የኖቭል ኮሮና ህመም” – ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም

“የህፃናት የኖቭል ኮሮና ህመም” – ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም

ታሪክ
ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሮና የተገኘው በ1937 ሲሆን ሰዎችን እንደሚያጠቃ የታወቀው ግን እአአ በ1960 መጨረሻ መሆኑ በታሪክ ይታወሳል። በ1970ዎቹ አካባቢ ደግሞ ስለ ኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች እና ስያሜ በደንብ የታወቀበተ ወቅት እና ሰፊ ጥናት የተደረገበት ጊዜ ነበር።

ሥያሜ
ኮሮና ማለት ከላቲን የተወረሰ ቃል ሲሆን ዘውድ ማለት ነው። ምክንያቱም በረቂቅ አጉይ መነፅር ሲታይ ክብ የሉል ቅርፅ ያለው ዙሪያውን ጥቃቅን ዘውድ የሚመስሉ ነገሮች ስላሉበት ነው። mid 6th century n corona : from Latin, ‘wreath, crown’.

ዝርያ
ኮሮና ቫይረስ ብዙ አይነት ዝርያዎች አሉት ። በግሪክ ፊደላት ዐልፋ ፡ ቤታ ፡ ጋማ እና ዴልታ የተመደቡ ዓይነቶች ሲኖሩ በብዛት በቀላል ጉንፋን አምጭነታቸው ይተወቃሉ። አስከፊ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች በቤታ ክፍል የሚመደቡ ሲሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ወረርሽኝ በማምጣት የሚታወቁት ኮሮና ቫይረሶች

የተቀሰቀሱበት ሀገር ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ይመስላል ፡
1 ፡ ሳርስ (SARS) 2003 እአአ ቻይና ፣
2 ፡ መርስ {MERS) 2012 እአአ ሳውዲ አረቢያ
3 ፡ ሳርስ 2 (COVID-19 ) 2019 እአአ ቻይና

ኮሮና ቫይረስ ብዙ እንስሳትን በተለይም የአጥቢ ዝርያዎችን፣ አእዋፋት እና ሰውን ጨምሮ ያጠቃል። በብዛት የሚታወቀው የሰው ጉንፋን አምጪ ኮሮና አብሮን የኖረ ሲሆን የከፋ የጤና እክል የማያስከትል ነው።

የከፋ የኮሮና ወረርሽኝ አምጪ ቫይረስ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፈው ከአጥቢ እንስሳት ጋር በተያያዘ ንክኪ (በተለይም የሌሊት ወፍ ) እና ጥሬ ስጋቸውን በመብላት መሆኑ ይታመናል። ቫይረሱ ራሱን መለዋወጥ እና እንደገና ማዋሃድ ስለሚችል በቀላሉ ከእንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋል።

የበሽታው መነሻ ሂደትና የህመም ምልክቶች

መነሻ
ክፉ እና አጣዳፊ የመተንፈሻ ህመም 2
በሳርስ ኮሮና ቫይረስ 2 (SARS 2 COVID-19) ምክንያት የሚከሰት የሳንባ ህመም ሲሆን ከአጥቢ እንስሳት ወደ ሰው በውሀን ቻይና መተላለፍ ጀመረ በመቀጠልም ከሰው መደ ሰው መተላለፍ ቀጠለ። ከዚያም ህመሙ ያለበት ሰው በሚያስል፣ በሚያስነጠስ ወይም በሚያወራ ሰዓት በሚፈጠሩ ውሃ አዘል ብናኞች ( aerosols) ወደ ሌላ ሰው አፍ፣ አፍንጫ፣ እና አይን ይገባል ከዚያም የቫይረሱ ተቀበይ ህዋሳት ባሉበት ከላይኛው ወደ ታችኛው የአየር መተላለፊያ ቱቦ ይወርድና በመጨረሻም የሳንባ የአየር ማጣሪያ ክፍልን ማጥቃት ይጀመራል።

ለኮሮና የሚጠቁ የሰውነት ክፍሎች
1 ፡ የመተንፈሻ አካላት
2 ፡ አንጀት እና ጉበት
3 ፡ የደም ስሮች
4 ፡ ኩላሊት
5 ፡ ስርዓተ ነርቭ

የበሽታው ምልክቶች መታየት የሚጀምሩበት ጊዜ

የኮሮና ህመም ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ከህመምተኛ ጋር ከተደረገ ንክኪ በኋላ ከ2 እስከ 14 ባሉት ቀናት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ እስክ 21 ቀናት ሊዘገዩ ይችላል። በአብዛኛው እስከ 5- 8 ቀን ድረስ ምልክት ማሳየት የጀምራሉ።

በብዛት የሚታዩ የህመም ምልክቶች
1 ፡ ከፍተኛ ትኩሳት 58% (አወቂ ላይ 81%)
2 ፡ ደረቅ ሳል 54% (አወቂ ላይ71%)
3 ፡ የትንፋሽ ማጠር 13% (አወቂ ላይ43%)
4 ፡ የድካም ስሜት ፡ የሰውነት መዛል
5 ፡ የሆድ ህመም

ብዙ ሕፃናት የህመም ምልክት አያሳዩም ምልክት ያለባቸውም ቢሆን መጠነኛ የሆነ የበሽታው ስሜት ይኖራቸዋል እንጂ አስጊ ምልክቶችን አያሳዩም። ሁሉም በሚያስብል ደረጃ ሕፃናት መታመማቸው የሚታወቀው በህመሙ የተጠቃ ቤተሰብ ሲኖር በጥርጣሬ የላቦራቶሪ ምርመራ ሲደረግላቸው ነው።

ለኮሮና በጣም ተጋላጭ እና ህመሙ የሚፀናባቸው ሕፃናት የትኞቹ ናቸው?
1 ፡ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት
2 ፡ የቆየ የልብ ፣ የሳንባ እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሕፃናት
3 ፡ በሽታን የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ ህፃናት
4 ፡ በምግብ እጥረት የተጎዱ
5 ፡ የካንሰር ታማሚዎች

ህፃናት ላይ የህመም ምልክቶች ለምን ቀለል ይላሉ?

1 ፡ ሕፃናት በዓመት ውስጥ ቢያንስ ከ4-6 ጊዜ በጉንፋን ይያዛሉ ከጉንፋን ቫይረሶቸ ውስጥ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ይገኙበታል ይህም ከኖቬል ኮሮና ቫይረስ በጥቂቱም ቢሆንም በሽታ የመከላከያ አቅም ይፈጥርላቸዋል።
2 ፡ ሕፃናት የኮሮና ቫይረስን የሚያከስሙ ንጥረ ቅመሞች በብዛት ስለሚያመርቱ።
3 ፡ ህፃናት በአየር ያልተበከለ እና ጠባሳ የሌለበት በሽታን የሚቋቋም የመተንፈሻ አካል ስላላቸው።
4 ፡ ንቁ የሆነ የበሽታን የመከላከያ ክፍል ስላላቸው።
5 ፡ የቆዩ እና ተጓዳኝ የጤና ችግሮች በህፃናት ላይ አለመብዛታቸው። ☺️

የላቦራቶሪ ምርመራ
1 ፡ ከአፍንጫ፣ ከአፍ እና ከመተንፈሻ አካላት ላይ ተጠርጎ የሚወስድ ፈሳሽ እና የአክታ ምርመራ
3 ፡ የራጅ ምርመራ
4 ፡ የሲቲ ስካን ምርመራ
5 ፡ እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምርመራ ሊደረግ ይችላል።

የኮሮና በሽታ ህክምና

ክትባት ወይም መድሃኒት የለውም ግን አንደ ህመሙ ቅለት እና ክብደት የሚሰጥ የህክምና አርዳታ አለ።
80% የሚሆኑት ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፋ ከሰው መለየት ጓንት እና ጭንብል መጠቀም እና የከፋ የህመም ምልክት እስካላሳዩ ድረስ ረፍት ማድረግ ብቻ በቂ ነው።

ተዛማጅ ለሆኑ የጤና እክሎች ህክምና ይደረጋል። የሙቀት መቀነሻ የኦክስጅን እርዳታ እና የመተንፈሻ አካላቸው ለተጎዱ ጽኑ ሕሙማን ሳንባን የሚያግዝ ወይም የሳንባን ስራ ተክቶ የሚሰራ ማሽን ያስፈልጋል።
በየእለቱ የሚያስፈልገውን ምግብ እና የጎደለ /የሚያስፈል ፈሳሽ መተካት።
የፀረ ተዋህስያን መድሃኒት።

ሞት
የህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመሞት እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው።

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ማስተማር ብቻ ነው። እንደባለ ሙያ የማውቀውን ካነበብኩት ጋር አስማምቸ ለህክምና ባለሙያ እና ለሁሉም እንዲስማማ አድርጌያለሁ። የሚጠቅም እና የሚያስተምር ከመሰላችሁ ማጋራት ይችላል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top