Connect with us

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አለፈ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አለፈ
Photo: Social media

ዜና

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አለፈ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አለፈ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩት ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አለፏል። ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ሁለት አድርሶታል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማምሻውን ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ህይወታቸው ያለፈው ሁለተኛው ግለሰብ የ56 ዓመት ወንድና የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ቀደም ሲል የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ አልነበራቸውም።

ግለሰቡ ከመጋቢት 24 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ በየካ ኮተቤ ሆስፒታል በጽኑ ህሙማን ክፍል በመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ የታገዘ ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ህይወታቸው እንዳለፈ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።

ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 47 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም አመልክተዋል።

የተፈጠረው ክስተት አስደንጋጭ ቢሆንም ተረጋግተን መመሪያዎችን በመከተል ችግሩን ልንከላከለው ይገባል ብለዋል።

( ኢዜአ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top