Connect with us

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ
Photo: Social media

ዜና

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ
~ በቫይረሱ የተያዙ ወገኖች ቁጥር 43 ደርሷል፣

የጤና ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና በሽታ (ኮቪድ-19) በቻይና ውሃን ከተማ ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ ወደ ሀገራችን ቫይረሱ እንዳይገባ እንዲሁም ከገባ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ቅስቀሳዎችን እያደረገና የተጠቂዎችን ቁጥርና የጤና ሁኔታቸው እያሳወቀ ነው፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 /2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22/2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያንስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በተያያዘ ዜና በላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል :: በአጠቃላይ ቁጥሩ 43 ደርሷል። (ጤና ሚ/ር)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top