Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህልውናውን ለማቆየት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህልውናውን ለማቆየት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል
Photo: Social media

አለም አቀፍ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህልውናውን ለማቆየት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 87 መዳረሻዎች የሚያደርጋችውን በረራዎች በግዜያዊነት ያቆመ ሲሆን፣ በመቀጠልም ወደተቀሩት መዳረሻዎች የሚያደርጋችውን በረራዎችም እያቋረጠ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አጥቷል። አየር መንገዱ ህልውናውን ለማቆየት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ ለመላው አፍሪካውያንና በፕላኔታችን ላይ ለሚገኙ ጥቁር ህዝቦች ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ውድቀት ይሆናል። አየር መንገዱ ከፊቱ ያጋጠመውን የፈተና ወጀብ በአስተማማኝ ድል አድራጊነት እንዲያልፍ የአየር መንገዱ ማኔጅመንትና ሰራተኞች ያለምንም የውጪ እገዛ በሰባቱም ቀናት 24 ሰዓት በከፍተኛ ትጋት በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ካለፈው ሰኞ መጋቢት 14 (March 23) ቀን ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በሙሉ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ በመደረጋችው ምክንያት ወደ ሀገራች የሚገቡ መንገደኞች ቁጥር ቀንሷል። በለይቶ ማቆያ ውስጥ የገባ ማንኛውም መንገደኛ የ14 ቀን የለይቶ ማቆያ የክትትል ግዜውን ሳያጠናቅቅ ከህብረተሰቡ ጋር ስለማይቀላቀል ቫይረሱ ቀጥታ ወደ ሀገራችን ይገባል የሚል ስጋት የለም። መንገደኞቹ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየረዳቸው ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል አስፈላጊ የህክምና መሳሪያዎችን እና አቅርቦቶችን ወደ ሀገራችን ያስገባ ሲሆን፣እነዚህን የህክምና ቁሳቁሶች ወደ ሀገራችን ለማስገባት ከአየር መንገዱ በስተቀር ሌላ ምንም አይነት አማራጭ የለም ፡፡ አየር መንገዳችን እስከ አሁን የኮሮናን ቫይረስ (ኮቪድ 19) ለመከላከል የሚረዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የህክምና አቅርቦቶችን ወደ ኢትዮጵያ ያጓጓዘ ሲሆን፣ አሁንም ይህን ተግባር አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አየር መንገዱ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያነት የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁሶችን በ 6 ቀናት ውስጥ ብቻ ለ 51 የአፍሪካ ሀገራት ያቀረበ ሲሆን፣ ህይወት አድን የሆኑትን እነዚህን የህክምና መሳሪያዎች ለኢትዮጵያ እና ለመላው የአፍሪካ አገራት ያደረሰ ብቸኛው አፍሪካዊ አየር መንገድ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ሲሆን፣ ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል በአውሮፕላኖቹ ውስጣዊ ክፍል፣ በእንግዳ ማረፊያ፣ እንዲሁም በሌሎች የስራ አካባቢዎች የኬሚካል ርጭት ስራ ይሰራል። ከዚህም ጎን ለጎን ለሰራተኞቹ እና ለአጋር ድርጅት ሰራተኞች የቫይረሱን መከላከያ ቁሳቁሶችን በመስጠት ላይ ይገኛል። የደንበኞቹን እና የሰራተኞቹን ደህንነት እና ጤንነት የሁልጊዜ ተቀዳሚ ተግባሩ በመሆኑ በእነዚህ ተግባራት ላይ ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል። ወደ ሀገሮቻቸው ተመላሽ የሆኑ መንገደኞችን ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ፣ ወደ አሜሪካ እና ካናዳ ያጓጓዘ ሲሆን፣ በርካታ ኢትዮጵያውያንንም በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል። በቀጣይም የኮሮናን ቫይረስ (ኮቪድ 19) መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ተለያዩ የሃገራችን ክልሎC ማድረሱን ይቀጥላል።

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top