Connect with us

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የሚፈጠር ጭንቀትን እንዴት መቀነስ እንላለን

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የሚፈጠር ጭንቀትን እንዴት መቀነስ እንላለን
(Celeste Romero Cano/Moment/Getty Images)

ነፃ ሃሳብ

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የሚፈጠር ጭንቀትን እንዴት መቀነስ እንላለን

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የሚፈጠር ጭንቀትን እንዴት መቀነስ እንላለን | በበሱፍቃድ ዜና

የኮሮና ቫይረስ በአለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ ብዙ ሰዎችን አጥቅቷል ከዛም አልፎ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎችን ለህልፈተ ሕይወት ዳርጓል፡፡ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎችን ለጭንቀት ዳርጓል፡፡

ብዙ ሰዎች በኮረና ቫይረስ የተነሳ እነሱ እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ለሞት እንዳይጋለጡ ይሰጋሉ፡፡ ይህም ሰዎችን ለጭንቀት ይዳርጋል፡፡በዚሕ ጽሁፍ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያገኘዋቸውን ጭንቀትን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶችን አቀርብላችኋለው፡፡

1.እራስን መንከባከብ
አቅም በፈቀደ መጠን የተመጣጠነ ምግብ እንመገብ ከአልኮል እና ሲጋራ ከመሳሰሉ ሱስ አምጪ ነገሮች እንራቅ፣በቂ እንቅልፍ እንተኛ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እናድርግ፡፡

2.እረፍት መውሰድ
በተቻለን መጠን ጭንቀታችንን ሊያስረሱን እና ዘና ሊያደርጉን የሚችሉ ነገሮች ላይ እናተኩር እንዲሁም በጥልቀት እንተንፍስ፡፡

3.ከሌሎች ጋር ይገናኙ
የሚያሳስቡንን ነገሮች ለጓደኛ ወይም ለቤተሰብ አባልዎ እናጋራ ፡፡ ይህን ሲያረጉ በሽታው በንክኪ እና በመቀራረብ የሚተላለፍ በመሆኑ አካላዊ እርቀቶትን መጠበቅ እንዳለቦት አይዘንጉ እንዲሁም እንደ ሞባይል እና ኢንተርኔት ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይጠቀሙ፡፡ ጸሎት ጭንቀትን የማስለቀቅ አቅም ስላለው ጭንቀታችንን ለፈጣሪ እንንገረው፡፡

4.ትክክለኛ የመረጃ ምንጫችን ይከታተሉ –
መረጃ እያጡ እንደሆነ ሲሰማዎት የበለጠ ውጥረት ወይም ጭንቀት ሊሰማዎት ይችላል። ከሚመለከታቸው አካላት የሚለቀቁ ዜናን ይመልከቱ ፣ ያዳምጡ ወይም ዜናውን ያንብቡ ፡፡ በንደዚ አይነት ጊዜ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ ወሬዎች ሊኖር እንደሚችል ልብ ይበሉ ፡፡ስለዚህ ሁል ጊዜ አስተማማኝ የመረጃ ምንጮችን ብቻ ይመልከቱ፡፡

5.ዜናዎች በተደጋጋሚ ከመመልከት ይቆጠቡ
መረጃዎችን በተደጋጋሚ ከመመልከት ፣ ከማንበብ ፣ ወይም የዜና ዘገባዎችን ከማዳመጥ እረፍት ይውሰዱ ፡፡ ስለ ቀውሱ መስማት እና ምስሎችን በተደጋጋሚ ማየት ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል። አስደሳች እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይሞክሩ እና በተቻለ መጠን ወደ መደበኛ ኑሮ ይመለሱ፡፡

ለበለጠ መረጃ human psychology@besufekadzena ላይክ ያድረጉ

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top