Connect with us

ለኮሮና መድሀኒት ለማግኘት ተስፋ ሰጪ ፍንጭ ታየ

ለኮሮና መድሀኒት ለማግኘት ተስፋ ሰጪ ፍንጭ ታየ
Photo Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ለኮሮና መድሀኒት ለማግኘት ተስፋ ሰጪ ፍንጭ ታየ

የኮሮና ቫይረስን ማዳን የሚችል መድሃኒት በኢትዮጵያ ለማግኘት መሰረታዊ የምርምር ሂደት ተሰርቶ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት ማለፉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ህክምና የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።

መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው ተብሏል፡፡

(ምንጭ፡- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top