Connect with us

ከሚልየነር ባለሀብቶች አንዱ የሆኑት ድንቁ ደያስ ወደአሜሪካን አገር መሸሻቸው ተሰማ

ከሚልየነር ባለሀብቶች አንዱ የሆኑት ድንቁ ደያስ ወደአሜሪካን አገር መሸሻቸው ተሰማ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ከሚልየነር ባለሀብቶች አንዱ የሆኑት ድንቁ ደያስ ወደአሜሪካን አገር መሸሻቸው ተሰማ

መንግስት ህግና ሥርዓትን ማስከበር በጀመረው መሠረት የሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ባለቤት አቶ ድንቁ ደያስ ንብረት የሆነው የሶደሬ መዝናኛ በኦሮምያ ክልል መንግሥት ትዕዛዝ ታሽጓል። ባለሀብቱ አቶ ድንቁ ደያስ ሸሽተው ወደአሜሪካን አገር ማቅናታቸው ተረጋግጧል።

አቶ ድንቁ ዛሬ ለንባብ ለበቃው አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ወደአሜሪካን አገር የሄዱት ለስራ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ሸሽተዋል መባሉን አስተባብለዋል።

ከ70 አመታት በላይ እድሜ የቆጠረው የሶደሬ መዝናኛ በኦሮሚያ ክልል ትእዛዝ መዘጋቱን አቶ ድንቁ ለጋዜጣው አረጋግጠው ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቁና ግፍ እየተፈፀመባቸው መሆኑን መናገራቸውን ዘግቧል።

አቶ ድንቁ ከለውጥ ሀይሉ ጀርባ የቆሙ ሀይሎችን ስፖንሰር በማድረግ በብርቱ ከሚጠረጠሩ ሰዎች አንዱ እንደነበሩ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ።

የለገደንቢ ሚድሮክ ወርቅ በአካባቢ ላይ ብክለት አስከትሏል በሚል በከፈሏቸው ግለሰቦች ተከታታይ ተቃውሞ ስፖንሰር በማድረግና በማነሳሳት ኩባንያው ያለስራ ከአንድ አመት በላይ ታግዶ እንዲቀመጥ በመንግስት ላይ ጫና ከማድረግ አልፈው ኩባንያውን ለመረከብ ብርቱ ፍላጎት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተናግረዋል።

የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ በአካባቢ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ በተመለከተ መንግሥት በካናዳ ኩባንያ ተገቢው ጥናት እንዲካሄድ አስደርጎ፤ ኩባንያው የተነሳበት ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑ ማረጋገጡና በጉዳዩ ላይ ጠ/ሚኒስትሩ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጡበት የጥናቱ ውጤት የቀረበላቸው መሆኑ ተረጋግጧል።

እነአቶ ድንቁ ካነሳሱት ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ኩባንያው በመዘጋቱ ከ400 ሚልየን ዶላር በላይ አገሪቷ የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ኩባንያውንም ለከባድ ኪሳራ መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው።

የሚድሮክ ባለቤትና ባለሀብት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ እንዲህ አይነት ዘርፈ ብዙ ጉዳት እየደረሰባቸውም እንኳን የአገራቸውን ጥቅም በማስቀደም በአዲስ አበባ ግዙፍ የዳቦ ማምረቻ እና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካዎችን በአጭር ጊዜ በመገንባት መንግስት የዋጋ ንረትን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በተለይ ለድሬቲዩብ ተናግረዋል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top