Connect with us

ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተገለፀ

ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተገለፀ
Photo Facebook

ዜና

ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተገለፀ

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳዩ 79 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ይህን ያስታወቀው የኮቪድ-19 ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው ዕለታዊ መግለጫው ነው፡፡

እንደመግለጫው ከሆነ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 16 ታማሚዎች መካከል ሁለቱ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን 14ቱ በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ መካከል አንድ ታማሚ በድጋሚ በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ መሆናቸው ቢረጋገጥም ለጥንቃቄ ሲባል ለ14 ተጨማሪ ቀናት በለይቶ ማቆያ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ማንኛውም መንገደኛ ለ14 ቀናት በሆቴል ውስጥ ተለይቶ እንዲቆይ ከተወሰነ ወዲህ ወደ ሀገሪቱ የገቡ 636 መንገደኞች በተመረጡ አስር ሆቴሎች ተደልድለው የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

ቀደም ሲል ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ የገቡ 873 ሰዎች ደግሞ በየቤታቸው ሆነው ለ14 ቀናት በጤና ባለሙያዎች በስልክ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

እነደዚሁም ለ14 ቀናት ተመሳሳይ የጤና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው የበሽታው ምልክት ያልታየባቸው 2,090 ሰዎች ክትትላቸው እንዲረቋጥ መደረጉ ታውቋል፡፡ #EBC

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top