Connect with us

ወርቁ አይተነው-ወርቅ ኾኖ ያየነው ኢትዮጵያዊ

ወርቁ አይተነው-ወርቅ ኾኖ ያየነው ኢትዮጵያዊ
Photo Facebook

ኢኮኖሚ

ወርቁ አይተነው-ወርቅ ኾኖ ያየነው ኢትዮጵያዊ

ወርቁ አይተነው-ወርቅ ኾኖ ያየነው ኢትዮጵያዊ
የ80 ሚሊዮን ኪራይ ሕንጻና የተሽከርካሪዎች ልገሳ ለኮሮና ቁጥጥር ድጋፍ
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ
እሳት የፈተነው ባለሃብት ነው፡፡ እንደ ስሙ በየቁርጥ ቀኑ ሲፈተን አልፏል፡፡ ለአማራ ተፈናቃዮች አለሁ ሲል ተደምጧል፡፡ የሞጣን መስጂድ ለማሰራት ሚሊዮኖች የለገሠ ሰው ነው፡፡ ወርቁ ችግር አለ ከተባለ የሚታይ ባለሃብት ነው፡፡ ተርፎት አይመስለኝም፤ ለመጎደል ያለውን ለመስጠት ወደኋላ አይልም፤ ችግሩ ሚሊዮኖችን ንቆ ሀገርና ወገን የሚያገዝፍ በመሆኑ ነው፡፡

ሰሞኑን ብዙ ቦታ ነበር፡፡ ለሀዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት ነበር፤ ለፋሲል ከነማ ነበር፡፡ ለባህር ዳር ከነማም እንዲሁ፡፡ በብዙ ግለሰቦች ህይወት ያደረገው ብዙ ነገር ተነግሮ አያልቅም፡፡ ዛሬ ደግሞ ከኮሮና መከላከሉ ጎን ሀገርን አለሁ አለ፡፡

ሰማኒያ ሚሊዮን አመታዊ ኪራይ ያለውን ህንጻ የኮሮና ቫይረስ በቁጥጥር ስር እስኪውል ሀገር ይጠቀምበት ዘንድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስረክቧል፡፡ አምስቱን አፓርታማዎች ሰጥቶ ዞር አላለም፡፡ ሁለት ቪ8 መኪኖችን ሁለት ሃይሩፍ ሚኒባሶችንም ጭምር ለዚሁ ተልኮ መስጠቱን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡

አቶ ወርቁ ከተመሰገነበት ያልተመሰገነበት መልካም ስራው የሚበዛ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት ነው፡፡ እስከአሁን በበርካታ ጉዳዮች ላይ ያለ ስስት ሲለግስ አይተናል፡፡ እርግጥ ነው ዘይትና ዱቄት ላይ ዋጋ የሚጨምር ክፉት በተንሰራፋባት ሀገር እንዲህ ያለው ለጋስ ኢትዮጵያዊ ከፍ ብሎ አይወደስም፤ መልካም የሰራው ስሙ የማይናኝባት ሀገር እንዲህ ሚሊዮን ብሮችን የሚለግሱ ቤታቸውን የሚያውሱ ደጋጎች ባሉበት ሀገር ዛሬም ዜጎች ዋጋ በሚጨምር ነጋዴ ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡
አቶ ወርቁ ግን የሚመሰገን ሰው ነው፡፡ ወርቅ ሆኖ አግኝተንዋል፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top