Connect with us

የትግራይ ክልል ጠንካራ ውሳኔ

የትግራይ ክልል ጠንካራ ውሳኔ
Photo Facebook

ዜና

የትግራይ ክልል ጠንካራ ውሳኔ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ፡፡

በትግራይ ከልል ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በ22 ዋና ዋና ጉዳች ላይ ከመከረ በኋላ ሶስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገ/ ሚካኤል/ዶ/ር/ አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ከገጠር ወደ ከተማ ፣ ከከተማ ወደ ገጠር፣ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረጉ ዝውውሮች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ታግደዋል፡፡

ህዝብ የሚበዛባቸው ገበያዎችም እንዳይካሄዱ መታገዳቸውንም ዶ/ር ደብረጽዮን ገልፀዋል፡፡

እንደ ሠርግና ተስካር ያሉ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችም ለጊዜው እንዳይካሄዱ የክልሉ ስራ አስፈጻሚ ወስኗል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት የተላሉፉት ውሳኔዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ተግባራዊ እንሚደረጉና በሽታው ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ እየተገመገመ የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ መናገራቸውን የትግራይ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
#Ebc

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top