Connect with us

እጅግ ጠቃሚ ምክር ~ ለጤና ሚኒስቴር

እጅግ ጠቃሚ ምክር ~ ለጤና ሚኒስቴር
Ethiopian Health Minister Dr Lia Tadesse./Photo courtesy of social media

ነፃ ሃሳብ

እጅግ ጠቃሚ ምክር ~ ለጤና ሚኒስቴር

እጅግ ጠቃሚ ምክር ~ ለጤና ሚኒስቴር
(ቅዱስ መሀሉ)

የጤና ሚንስቴር እና የህዝብ ጤና ጥበቃ ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎችን የሚይዝበት እና የሚመረምርበት አሰራር በድጋሚ ሊጤን ይገባዋል። እስካሁን በጥቆማ ተያዙ እየተባሉ ወደጤና ጣቢያ ከተወሰዱ እና ወደ ሆፕሲታልም የሄዱትን መርምረው የለባችሁም ብለዋል። በባህር ዳርም ዘጠኝ ሰዎች ተጠርጥረው በምርመራ የኮሮና ቫይረስ የለባችሁም ተብሏል።

ይህ የተጠረጠረውን ሁሉ የመመርመር አሰራር በኢትዮጵያ አቅም አይደለም በአሜሪካ፣ በካንዳ፣ በጀርመን እና በእንግሊዝ ወዘተ አቅም እንኳ በአሁን ሰዓት ስራ ላይ አልዋለም። መመሪያው ራስህን ከጠረጠርክ በቤትህ ለቀናት አስታም ነው። ሳል እና ትኩሳት ሊገለኝ ነው ብለህ ብትደውል እንኳ “እዚህ ደግሞ መተንፈስ አቅቷቸው መቃብር አፋፋ ላይ የቆሙ አሉ። ቅድሚያ ለነሱ ነው።” ነው የሚባለው። ምክንያቱም ያላቸው የመመርመሪያው ቁስ መጠን እና በኮሮና ቫይረስ የሚያዘው ህዝብ ቁጥር የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለው። የሕዝብ ጥበቃ ጤና ተቋማት ያሉት የኮሮና ምልክት የታየበት ሰው ለቀናት በቤቱ ራሱን እና ቤተሰቡን እንዳይበክል በማስክ እየጠበቀ እና በቤት ውስጥ ለጉንፋን ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች እያደረገ እንዲቆይ ነው። መርምሩኝ ላለ ሁሉ የበሽታው ምልክት ቢኖርበትም እንኳ ባንዳንድ ስፍራ እጥረቱ ከፍተኛ ስለሆነ አይመረመርም።

የበሽታው ምልክት ኮሮና ቫይረስ ቢሆን የማያገግም ከሆነ እና ከባሰበት ሰውየው የትንፋሽ እጥረት ይገጥመዋል። እዚያ ደረጃ ላይ ሳይደር ቢመረመር እና ኮሮና ቢገኝበት እንኳ ራስህን ቤትህ አስታም ተብሎ ይመለሳል እንጅ እንጅ የሆስፒታል አልጋ አይሰጠውም። ምክንያቱም ሆስፒታሎች የተዘጋጁት እና ዝግጁ ሆነው በአሁን ሰዓት የሚጠብቁት የትንፋሽ እጥረት ገጥሟቸው የኦክስጅን እገዛ የግድ የሚያስፈልጋቸው በሽተኞችን ነው።

የኔ ጥያቄ የጤና ሚንስቴር በእርዳታ ያገኘውን 10ሽ ሰዎችን እንኳ ለመመርመር የማይበቃ ቁስ ጠረጠርኩ እያለ ትኩሳት ያለበትን እና የሳለውን ሁሉ ለመመርመር ከተጠቀመበት ዋናው ወጀብ ሲመጣ ምን ሊውጠው ነው? እንዲያው የጤና ሚኒስቴር ከቻለ በሆነ ሃገርኛ ጥበብ ተጠቅሞ አንዷን መመርመሪያ እንዴት ለ5 ለ6 ሰው ሊጠቀምባት እንደሚችል ማሰብ እንጅ አሁን ባለው አሰራር ከተገኘባቸው ሰዎች ይልቅ ጠረጠርኩ ብሎ ነጻ ያላቸውን ሰዎች ስናስብ ውስን በእርዳታ የተገኙ መመርመሪያ ቁሶችን እያባከነ ነው ማለት ይቻላል። የጤና ሚኒስቴር እና የህዝብ ጤና ጥበቃ ተቋም አሰራር መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ እና ከዓለም አሰራር ጋርም የሚጋጭ ነው። ያው ይታረም ለማለት ነው።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top