Connect with us

ለዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነዋሪዎች የቀረቡ ጠቃሚ መረጃዎች:-

ለዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነዋሪዎች የቀረቡ ጠቃሚ መረጃዎች
FILE - In this March 19, 2020, file photo, the Manhattan bridge is seen in the background of a flashing sign urging commuters to avoid gatherings, reduce crowding and to wash hands in the Brooklyn borough of New York. The coronavirus pandemic is leading to information overload for many people, often making it difficult to separate fact from fiction and rumor from deliberate efforts to mislead. (AP Photo/Wong Maye-E, File)

ጤና

ለዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነዋሪዎች የቀረቡ ጠቃሚ መረጃዎች:-

አንዳንድ የዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ የግዛቲቱ አስተዳደር ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ይህንን ተከትሎ በወጡ ህጎች መሰረት ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው ተለይተው፣ የንግድ ተቋማትም ተዘግተው እቤት በመዋል የቫይረሱን ስርጭት እየተከላከሉ ቢሆንም ኑሮአቸው በምን መልኩ እንደሚቀጥል እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል:: ይህንን መሰረት በማድረግ የሚከተሉ መረጃዎች ቀረበዋል:-

1) በዲስትሪክቱ ስለበሽታው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት: www.coronavirus.dc.gov ይጫኑ፣

2) በዲስትሪክቱ በልዩ ሁኔታ እስከ ኤፕሪል 27/2020 ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑ ተቋማትን ለማወቅ: www.coronavirus.dc.gov/page/whats-open ይጫኑ፣ ለምሳሌ የቆሻሻ አወጋገድ በተለመደው መልኩ እንደሚቀጥል፤ የመኪና ማቆሚያ ቅጣት የእሳት አደጋ መከላከያ ሃይድራንትን ከመከለል ውጪ ሌላው ለጊዜው እንደማያስቀጣ፤ የንግድ ፈቃድ ኦንላይን በ: www.business.dc.gov በመጫን ማሳደስ እንደሚቻል፣

3) ከስራ የተፈናቀሉ ሰዎች ጥቅማጥቅምና ከስራ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለማግኘት: www.dcnetworks.org/vosnet/Default.aspx ይጫኑ፣

4) የአሜሪካ ኢኮኖሚ ብሎም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መሰረቱ አነስተኛ ቢዝነሶች ስለሆኑ እነዚህ ተቋማት በኮሮና ቫይረስ ስጋት በመዘጋታቸው የደረሰባቸውን ጉዳት ለመቀነስና ዳግም እንዲጠናከሩ የፌዴራል መንግስት ከከፈተው የብድር ዕድል ለመጠቀም: www.coronavirus.dc.gov/recovery-business በመጫን መመልከትና www.sba.gov/funding-programs/disaster-assistance በመጫን ማመልከት ይችላሉ::

5) በአስቸኳይ ጊዜ አወጁ ወቅት የቤት ኪራይ፣ የኤሌክትሪክ፣ የጋዝ እና የውሃ ክፍያ መጠየቅም ሆነ ማቋረጥ የማይቻል መሆኑን፣ የዲ.ሲ. ፐብሊክ ትምህርት ቤቶቸ የነጻ ምገባ የሚሰጥ መሆኑን፣ ዝርዝሩን (202) 727 5355 በመደወዕል መጠየቅ ይቻላል፣

6) ማደሪያ ለሌለው ጊዜያዊ የመጠለያ አገልግሎት ለማግኘት (202)399 7093 ወይም 311 መደወል ይቻላል፣

በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አደረጃጀቶች ለየአካባቢው ተስማሚ የሆነ መረጃ በማቅረብ ህብረተሰቡን እንድታግዙ ከአደራ ጭምር እጠይቃለሁ::

እነዚህንና ሌሎች ወቅታዊ መረጃዎችን በመጠቀም ራሳችሁን ከበሽታው እየጠበቃችሁ ቀጣይ ኑሮአችሁ እንዲቃና መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ::

@አምባሳደር ፍፁም አረጋ

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top