Connect with us

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የሚፈጠር ከልክ ያለፈ ጭንቀትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የሚፈጠር ከልክ ያለፈ ጭንቀትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?
Photo Facebook

ነፃ ሃሳብ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የሚፈጠር ከልክ ያለፈ ጭንቀትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ በሰዎች ዘንድ እየፈጠረ ያለዉ ጨንቀትና መረበሽ እየጨመረ ይገኛል፡፡

ጆሴፍ ማክጉሬ በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ሳይኮሎጅስት ናቸዉ፡፡ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ተከትሎ የሚፈጠር ጭንቀትና መረበሽ አንዴት መቀነስና መቆጣጠር ይቻላል በሚሉት ሀሳቦች ላይ የሚከተሉትን ምክሮች አጋርተዋል፡፡

ዝግጁ ሁኑ፤ አትረበሹ

በማህበራዊ ሚዲያ ስለኮሮና ቫይረስ በርካታ መረጃዎች ይሰራጫሉ፡፡ በተለይ አሁን ባለንበት መረጃዎች በፍጥነት በሚለዋወጡበት ወቅት በእነዚህ መገናኛ ዘዴዎች የሚወጡ አብዘሀኛዎቹ መረጃዎች የተሳሳቱ፤ የተዛቡ ወይንም የተጋነኑ ናቸዉ፡፡

ዶክተሩ እንደሚሉት ከሆነ ከተዓማኒ ምንጮች የሚወጡ ስለቫይረሱና ራስን መከላከል ስለሚቻልባቸዉ መንገዶች ወቅታዊና ሳይንሳዊ መረጃዎችን ብቻ በመዉሰድ፡፡ ለምሳሌ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅትና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት የሚያሰጧቻን መመሪዎችን መከተል፡፡

ስለቫይረሱ የሚኖረን ዕዉቀትና ዝግጁነት ጭንቀትን ለመቀነስ እንደሚረዳ ይመክራሉ ጆሴፍ ማክጉሬ፡፡ እንደ ዶክተሩ ሀሳብ ከሆነ ወረርሽኙን በተመለከተ የትኛዉንም ተግባር ለመፈፀም፤ የግል ዕቅዶችን ለማዉጣትም ሆነ ለመተግበር የታመኑ የመረጃ ምንጮችን ብቻ መከተል ተገቢ ነዉ፡፡

ወደ ቀልብዎ ይመለሱ

ጭንቀት በሽታ የመከላከል አቅምን ይጎዳል፡፡ ምንም እንኳን እንዲህ ያለ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ጭንቀት ለኮሮና ቫይረስ የማጋለጥ እድል እንዳለዉ ማረጋገጫ ባይገኝም፡፡ ጭንቀትዎን ጤናማ በሆነ መልኩ ለመቀነስ የሚያግዙ ተግባራትን መከወን ጠቃሚ ነዉ፡፡ በማለት ይናገራሉ፡፡

ጨንቀትንና መረበሽኝ ለመቀነስ አንዱ መንገድ ወደ ቀልብ በመመለስ ነባራዊ ሁኔታዉን በመረዳት መጀመር ነዉ፡፡ ጆሴፍ እንደሚሉት እንዲህ ባሉ አስቸጋሪ ወቅቶች ወደ ቀልብ መመለስና ራስን ማረጋጋት ወሳኝ ብልሀት ነዉ፡፡ የተፈጠረዉን ነገር መቀበልና ይገባል፡፡ ፀጥ ያለ ቦታ ቁጭ በማለት ሙሉ ትኩረትን ወደ ራስ በማድረግና ራስን ማረጋጋትን መለማመድ ያስፈልጋል፡፡

ሌላዉ ጭንቀትን የምንቀንስበት መንገድ ለኮምፒዩተር፤ ለሚዲያዎች ያለንን ተጋለጭነት በመቀነስ ነዉ፡፡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ማግኘት በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡ የምንሰጠዉ ትኩረት ከልክ ሲያልፍ ደግሞ ጉዳት እንዳለዉ በመግለፅ ዶክተሩ ያስጠነቅቃሉ፡፡ ነገሮች ከልክ እንዳያልፉ ገደብ ማበጀት በሁኔታዎች ከመደናገጥና ከመረበሽ ያድናል፡፡

በመጨረሻም ጆሴፍ እንዲህ ይላሉ “እባካችሁ ፍርሀት እንዲቆጣጠራችሁ አትፍቀዱለት

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top