Connect with us

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ጥብቅ መመሪያ አወጣ

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ጥብቅ መመሪያ አወጣ
Photo Facebook

ጤና

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ጥብቅ መመሪያ አወጣ

በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ኘረዝደንት ኘሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ፊርማ በዛሬው ዕለት የወጣው መመሪያ በርካታ ክልከላዎችን ይዟል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጣው መመሪያ ከያዛቸው ክልከላዎች መካከል ማንኛውም ተማሪ ከግቢ መውጣት እንደማይፈቀድለት የሚጠቅሰው ይገኝበታል። እወጣለሁ የሚል ተማሪ ካለ ተመልሶ እንደማይገባ ተደንግጓል።

በተጨማሪም ማንኛውም ተማሪ ከከተማ ወደግቢ መግባት የተከለከለ ሲሆን ወደግቢ መግባት የሚፈቀደው አስፈላጊውን የኮሮና ህመም ምርመራ ተደርጎ ጤንነቱ ከተረጋገጠ ብቻ ነው ይላል።

እንዲሁም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በጋራ ስፖርት መስራት፣ ተሰብስቦ ቴሌቭዥንና ዲኤስቲቪ መመልከት ተከልክሏል።

በተጨማሪም ሙዚየም እና ኦብዞርቫቶሪ ለተማሪዎችና ለጎብኚዎች ዝግ መደረጉን የጠቀሰው መመሪያው ከተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ በስተቀር ሌሎች ካፌዎች ዝግ ይሆናሉ ብሏል።

(የመመሪያውን ሙሉ ቃል ከደብዳቤው ያገኛሉ)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top