Connect with us

የእጅ ስልካችንን በማጽዳት ራሳችንን እንዴት ከኮሮና ቫይረስ መከላከል እንችላለን

የእጅ ስልካችንን በማጽዳት ራሳችንን እንዴት ከኮሮና ቫይረስ መከላከል እንችላለን
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የእጅ ስልካችንን በማጽዳት ራሳችንን እንዴት ከኮሮና ቫይረስ መከላከል እንችላለን

በቤታችንም ሆነ በምንሰራበት ስፍራ በተደጋጋሚ የእጅ ንክኪ የሚበዛባቸው ስፍራዎችን ማጽዳት ከቫይረሱ የመከላከያ መንገዶቹ መካከል አንዱ ነው።

ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል አደገኛ ተህዋሲያንን (ጀርሞችን) ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? በኮሮና ቫይረስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት?

ስልካችንን ለማጽዳት 70 በመቶ አልኮል ያለው ዋይፐር መጠቀም የሚቻል ሲሆን በረኪና ግን አይመከርም። ቀላል ሳሙናና ውሃም ለማጽዳት እንደሚያገለግልም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ማይክሮባዮሎጂስት የሆኑት ዶ/ር ሌና ሲሪክ ስልክዎን ለማጽዳት ከቻርጀሩ መንቀል፣ መሸፈኛ ካለው ማውለቅ ቅድሚያ ልትወስዷቸው የሚገባው ዋንኛ ተግባር መሆን አለበት ሲሉ ይመክራሉ፡፡

ዋና ዋና የሚባሉት የስልክ አምራቾች ስልካችንን ለማጽዳት ኬሚካሎች፣ ለእጃችን ማፅጃነት የምንጠቀምባቸው ሌሎች የጽዳት መጠበቂያዎች፡፡እንዲሁም ሸካራ ነገርን ለማጽዳት የሚያገለግሉ ዋይፐሮችን መጠቀምን አይመክሩም።

ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው የስልክዎን ስክሪን መከላከያ ይጎዳሉ አልያም ያወድማሉ የሚል ነው። ስለዚህ በቀላሉ በውሃና በሳሙና በተነከረ ጥጥ ወይም ከጥጥ በተመረተ ጨርቅ ማጽዳት በቂ መሆኑን ዶ/ር ሌና ይናገራሉ።

በጥጥ ወይም በጨርቁ የስልክዎን ስክሪንም ሆነ ጀርባ እንዲሁም ጎኖች ማጽዳት ይችላሉ። በዚህ ወቅት ግን የሚያጸዱበት ፈሳሽ በስልኮቹ ክፍተቶች በኩል እንዳይገባ ጥንቃቄ ያድርጉ።

በርግጥ አንዳንድ ውሃን የሚቋቋሙ ስልኮች ቢኖሩም ከጊዜ በኋላ ግን ይህንን ብቃታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በአግባቡ ከወለወሉ በኋላ በለስላሳ ጨርቅ ማድረቅ አይርሱ።

አይፎንን ስልኮችን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ አፕል ስልክዎን በአግባቡ 70 በመቶ አይሶፕሮፔል አልኮል ባላቸው ዋይፐሮች ማጽዳት እንደሚችሉ ይመክራል። እነዚህን ዋይፐሮች የኮምፒውተር መለዋወጫዎች መሸጫ ሊያገኟቸው ይችላሉ።

በዚህ ሁሉ ስልክዎን ካፀዱ በኋላ ባልታጠበ እጅዎ ከሆነ የሚጠቀሙት መልሶ ስልክዎ በጀርሞች ይሞላል። ስለዚህ እጅዎን በየጊዜው መታጠብ አይርሱ! መረጃው ከቢቢሲ የተወሰደ ነው፡፡

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top