Connect with us

መንግሥት የሚገራበት መንገድ ከሌለ የትም መድረስ አይቻልም – ፕሮፌሰር አየለ ትርፌ (ክፍል 1)

መንግሥት የሚገራበት መንገድ ከሌለ የትም መድረስ አይቻልም - ፕሮፌሰር አየለ ትርፌ (ክፍል 1)

ፓለቲካ

መንግሥት የሚገራበት መንገድ ከሌለ የትም መድረስ አይቻልም – ፕሮፌሰር አየለ ትርፌ (ክፍል 1)

ፕሮፌሰር አየለ ትርፌ ወ/ሚካኤል ከ25 ዓመታት በፊት ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ በህወሓት/ኢህአዴግ ከተባረሩት 42 ምሁራን አንዱ ነበሩ፡፡ በወቅቱ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚደንትም ነበሩ፡፡ በምን ምክንያት እንደተባረሩም እስካሁን በትክክል ሳያውቁ ቆይተው ከለውጡ ጋር ተያይዞ እንደገና ወደዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ለማስተማር ዕድል ካገኙት ምሁራንም አንዱ ሆነዋል፡፡

የኢኮኖሚ ባለሙያው ፕሮፌሰር አየለ በአክራሪ ብሔርተኞችና ሃይማኖተኞች እየተፈጠሩ ስለሚገኘው ሁኔታ ስናነሳላቸው በአጭሩ “እየተዋጉ፣ እየተባሉ ማደግ አይቻልም…በኢትዮጽያ ስም አንድ ሆኖ መሥራትን የመሰለ ለዕድገት ሞተር የለም” ብለውናል፡፡ አሁን በተጨባጭ ያለው የተቆራረጠ ሁኔታ የትም እንደማያደርስ በመግለጽ መፍትሔው በአንድነት መቆም ነው ይሉናል፡፡ ሁለት ዓመታት የቆጠረውን የለውጥ ሒደት አስመልክቶም በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዘመን “ይኸቺ አገር” ከመባል “ኢትዮጵያ” መባል ጀምረናል ብለዋል፡፡

እርጋታ፣ ብስለት፣ ጥልቀት ያለውን የፕሮፌሰሩ ቃለምምልስ ክፍል አንድ እነሆ አጋርተናል፡፡ በክፍል ሁለት ስለአገሪቱ ኢኮኖሚ ያጋሩንን ይዘን እንመለሳለን፡፡ መልካም ቆይታ፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top