Connect with us

“በአባይ ወንዝና በግድቡ ዙሪያ ለየትኛውም ጫና አንበረከክም” – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

“በአባይ ወንዝና በግድቡ ዙሪያ ለየትኛውም ጫና አንበረከክም” - አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
Photo: Facebook

ዜና

“በአባይ ወንዝና በግድቡ ዙሪያ ለየትኛውም ጫና አንበረከክም” – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

“በአባይ ወንዝና በግድቡ ዙሪያ ለየትኛውም ጫና አንበረከክም” –  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢፊዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

የአባይ ወንዝ የመጠቀም ተፈጥሮአዊ መብታችንን በማደናቀፍ በግደቡ ዙሪያ የሚደረግ ጫና ተቀባይነት የለውም፤ እኛ ለየትኛውም ጫና አንበረከክም” ሲሉ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአልጄዚራ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለ ምልስ እንደተናገሩት፤ ግድቡ ስራ ሲጀምር በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ጉዳት እንዳያስከትል ለመከላከል የውሃ መሙላት ተግባሩን በደረቅ ወቅት ለመሙላት እና ሃይል ካመነጨ በኋላ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ከግድቡ ወደ ታችኛው ተፋሰስ እንዲወርድ አገራቱ ተስማምተዋል፤ ግብጾችም ይሄንን በደንብ ያውቃሉ፣ ግን አሁንም ህዝባቸውን በኢትዮጵያ ላይ ለማነሳሳት መርጠዋል።

እንደ አቶ ገዱ ማብራሪያም፤ ኢትዮጵያ አባይ ከምድሯ እንደሚፈልቅ ብታውቅም የሱዳን እና የግብፅ ፍላጎት እንዲሁ ሊጠበቅላቸው ይገባል የሚል እምነት አላት። ለሶስቱ አገራት ህዝቦች ሕይወት የሚሰጥ አባይ በተፋሰሱ ለሚኖሩ ለሁሉም ህዝቦች የህይወት መድህን ሆኖ ይቆያል። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ጫና ካለ መንግስት ለየትኛውም ወገን ጫና አይንበረከክም።

በአባይ ተፋሰስ አገሮች መካከል በትብብር መርህ ላይ የተመሠረተ አዲስ ራዕይ ማቋቋም እንፈልጋለን ያሉት አቶ ገዱ፤ “እኛ የግብፅን አሳሳቢ ጉዳዮች እናውቃለን። በእርግጥ ኢትዮጵያ የግብጽን ህዝብ የመጉዳት ዓላማ የላትም። መንግስት ድህነትን ከኢትዮጵያ ለማስወገድ ጥረት እያደረገ የግብጽ ህዝብ እንዲደኸይ አይፈልግም” ሲሉም መንግስት በጋራና በፍትሃዊ ተጠቃሚነት ላይ ያለውን አቋም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ሁሉም የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት ከወንዙ ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ታምናለች ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ “እኛ ሰላም ፈላጊ ነን፣ እኛ የምንፈልገው ነገር ግድቡ በሌሎች ላይ ጉዳት ሳያስከትል ድርሻችንን ማግኘት ብቻ ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ ሁሉንም የግድቡን ዲዛይኖች ለሱዳን እና ለግብጽ አስተያየት እንዲሰጡበት አስገብተናል፤ ጉዳት እንደሌለው ያውቃሉ” ነው ያሉት።

“የግብጽ ሚዲያዎች ስለ ህዳሴው ግድብ ሁሉንም ዝርዝር ነገሮች ያውቃሉ፤ ውሃው ኤሌክትሪክ ካመነጨ በኋላ በሙሉ ወደ ወንዙ እንደሚመለስና እንደ ድሮው ወደ ግብጽ እንደሚፈስም ያውቃሉ፤ ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን የናይል ውሃን በጭራሽ እንዳይጠቀሙ፤ ስለመጠቀም እንኳ እንዳያስቡ የሚከለክል ድምጸት ያለው ዘመቻ ከፍተዋል፤ ይህ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው እና ፍትሃዊም አይደለም”።

ግብፃውያንም የኢትዮጵያዊያንን የልማት ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ አለማስገባታቸው እና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘላለማዊ ድህነት ውስጥ እንዲቆዩ መፍረድ ሰብአዊ አይደለም በማለትም ነው አቶ ገዱ በግብጽ ወገን ያለው አቋምና አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለው የተናገሩት። (ኢ.ፕ.ድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top