Connect with us

አየር መንገዱ አስተባበለ

አየር መንገዱ አስተባበለ
Photo: Facebook

ዜና

አየር መንገዱ አስተባበለ

በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ለሚገኙ ሀሰተኛ ፅሁፎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫ

ውድ ደንበኞቻችን አንዳንድ ግለሰቦች ማህበራዊ ሚድያን በመጠቀም ፍፁም ከእውነት የራቀ መረጃን ህብረተሰቡን ለማደናገር በማውጣት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ በአህጉራችንም ሆነ ባጠቃላይ በአለማችን ብዙ አየር መንገዶች እየበረሩ መሆናቸው እየታወቀ የኢትዮጸያ አየር መንገድ ብቸኛ በረራ ያለው አየር መንገድ በማስመሰል በአየር መንገዱ ላይ የስም ማጥፋት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። በተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ ግን አየር መንገዶች ለምሳሌ፦ የኬንያ አየር መንገድ፣ የኤመሬትስ አየር መንገድ፣ የህንድ አየር መንገዶች፣ የሲንጋፖር አየር መንገድ ፣ የሞሮኮ አየር መንገድ፣ የቱርክ አየር መንገድ እና ሌሎችም አየር መንገዶች መብረራቸውን ቀጥለዋል። ወደ አዲስ አበባም ከአስር የሚበልጡ አየር መንገዶች መብረራቸውን ቀጥለዋል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ህብረተሰቡን ባልሆነ መረጃ እያሳሳቱ ይገኛሉ።

በተደጋጋሚ አንደ ተባለው የኢትዮጸያ አየር መንገድ የአለም ጤና ድርጅት እና የአለም የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ባወጡት መመሪያ መሰረት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ በረራውን ወደ ተለያዩ አገሮች እያካሄደ ይገኛል።

በቅርቡ የተመለከትነው በፍፁም የተሳሳተ መረጃ አየር መንገዱ ከስሮ ሊዘጋ እንደሆነና በሰራተኞቹ አድማ እንደተደረገ አስመስለው የበሬ ወለደ አይነት ውሸት ያወጡ ግለሰቦች እንዳሉ ተመልክተናል። ሆኖም ለውድ ደንበኞቻችን ማሳወቅ የምንፈልገው ምንም እንኳን የኮሮና ቫይረስ (COVID 19) በአለም አየር መንገዶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አለም አቀፍ ቀውስ በትጋት እና በፅናት ከመላው ታታሪ እና ጠንካራ ሰራተኞቹ ትብብር በስኬታማ ሁኔታ እየተወጣው ይገኛል፡፡

የምትወዱት እና የምትሳሱለት አየር መንገዳችሁ አሁንም በጠንካራ እና በስኬታማነቱ የተፈጠረውን አለም አቀፋዊ የኮሮና ቫይረስ ተግዳሮቶች የእናንተም የውድ ደንበኞቹ ድጋፍ ተጨምሮበት ስራዎቹን በሙሉ አንደተለመደው በጥንቃቄ እና በትጋት እየቀጠለ እንደሚገኝ ያሳውቃል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top