Connect with us

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት በከፊል ዝግ ይሆናሉ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት በከፊል ዝግ ይሆናሉ
Photo: Facebook

ዜና

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት በከፊል ዝግ ይሆናሉ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ በመንግስት በኩል የኮሮናን ሥርጭት ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ሲሆን በቀን ከ18 ሺ በላይ አገልግሎት ፈላጊዎችን የሚያስተናግዱት የፌደራል ፍርድ ቤቶችን በከፊል ዝግ ማድረግ ተቋሙ ያደረገው እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ካለባቸው ተቋማት ውስጥ የሆኑት ፍርድ ቤቶች በአንድ ክስ ምክንያት እስከ 600 ሰዎች በአንድ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ መሆኑንና ከ50 በላይ ምስክር የሚያስፈልጋቸው ከባድ የክስ መዝገቦችም ስላሉ የበሽታውን ስርጭት በቀላሉ ሊጨምረው ይችላል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ፍርድ ቤቶችን በከፊል ለመዝጋት የተወሰነው የበሽታውን ስጋት ማስቀረት ባይቻል እንኳን ለመቀነስ መሆኑን ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ይሆናሉ የተባለው ከነገ መጋቢት 10 እስከ መጋቢት 24 ሲሆን ቀጠሮ ያላቸው መዛግብት በ2 ቀናት ውስጥ የቀጠሮ ለውጥ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡

የቀጠሮ ለውጥ ያለው ባለጉዳይ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እንዲሁም በአካል ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመምጣት የቀጠሮውን ለውጥ መመልከት ይችላል ብለዋል፡፡

ነገር ግን ፕሬዝዳንቷ እባካችሁ ወደ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ለውጥ ለማየት ስትመጡ የሰዎችን መጨናነቅ ለመቀነስ ብቻችሁን እንድትመጡ ብለዋል፡፡

በከፊል ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ዝግ ይሆናሉ የተባሉት ፍርድ ቤቶች፣ በአገር ፀጥታና ደህንነት ጋር የተገናኘ ጉዳይን ግን ይመለከታሉ ተብሏል፡፡(ሸገር ራዲዮ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top