Connect with us

አንሸበር! እንጠንቀቅ!

አንሸበር! እንጠንቀቅ!
Illustration: Guardian Design/EPA/GETTY

ጤና

አንሸበር! እንጠንቀቅ!

አንሸበር! እንጠንቀቅ!

ኮሮና ቫይረስ አፍሪካን ማመስ ጀምሯል። ኬንያ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተገኘባት ከምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያዋ ሀገር ስትሆን ኢትዮጵያም ተከትላታለች፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ጃፓናዊ ተገኝቷል።

አሁን ላይ ዓለምን እያዳረሰ ያለው የቫይረሱ ወረረሽኝ ኢትዮጵያም ውስጥ ተገኘ ብሎ ያለቅጥ መሸበር አይጠቅመንም።

ምን እናድርግ?
__________________

1.እጃችንን እንታጠብ
አዘውትረን በሳሙና እና በውሃ ለሀያ ሴኮንድ እጆቻችንን አዘውትረን እንታጠብ።

2.መጨባበጥ ይቅር

3. ሰው ከሚሰበሰብበት እንራቅ።

4. እንሸፈን:- በሚያስለን ወይንም በሚያስነጥሰን ግዜ ፊታችንን በክንዳችን ወይም በመሸፈኛ እንሸፍን።

5. ፊታችንን አንነካካ።

6. የጋራ መገልገያዎችን አንነካካ:- ብዙ ሰው የሚነካካቸውን ነገሮች ማለትም የበር እጀታዎች፣ የደረጃ መደገፍያዎች እና የመሳሰሉትን አንነካካ። ምናልባት ከነካን እጅን በሳሙና መታጠብን አንርሳ።

7. ነጻ የስልክ መስመር: የበሽታው ምልክቶች ከታዩብን 8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል አንርሳ።

አስታውሱ!
ወረርሽኙን ማቆም ባንችል እንኳን ፍጥነቱን መቀነስ እንደምንችል አንዘንጋ።
በተለይ …
__________________

ወጣቶች በበጎ ፈቃድ በየቦታው ተደራጅታችሁ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ህብረተሰቡን እናግዝ።

የእምነት ተቆማት የስብከት እና የአምልኮ መርሐ ግብሮቻችሁን ለምእመናኖቻችሁ ጤና ቅድሚያ በመስጠት ላልተወሰኑ ጊዜያት ብታስተላልፏቸው።

መንግስት ቫይረሱ ብሔራዊ አደጋ መደመሆን እንዳይሸጋገር የላቦራቶሪ እና የለይቶ ማቆያዎች አቅሙን በአፋጣኝ መገንባት ቢችል

ከፈጣሪ ጋር ጥንቃቄ አይለየን!
_________________

አጋሩት! share it !

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top