Connect with us

ኢትዮጵያዊያኖች በደቡብ ኮርያ ደም ለገሱ

ኢትዮጵያዊያኖች በደቡብ ኮርያ ደም ለገሱ
Photo: Facebook

ጤና

ኢትዮጵያዊያኖች በደቡብ ኮርያ ደም ለገሱ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ደም የሚለግሱ ሰዎች በታጡበት ደቡብ ኮርያ ኢትዮጵያዊያኖች ደም ለገሱ።

የደም ልገሳውን ያደረጉት በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አንድ የደቡብ ኮርያ የዜና ምንጭ አስታውቋል።

በጎ ፈቃደኞቹ ይህንን ተግባር ያደረጉት ሌሎች የውጭ ዜጎችን ከማበረታታት ባለፈ ደቡብ ኮርያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የተለየና የጠበቀ ግንኙነት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

“በታሪክ ኢትዮጵያና ኮርያ የራሳቸው ትዝታ አላቸው ፤ ይህም እንደ አውሮፓውያኑ በ1952 ኢትዮጵያዊያን አባቶቻችን እዚህ መጥተው ተዋግተዋል፤ እኛም ይህንን ማስቀጠል እንፈልጋለን” ሲል ተናግሯል ከደም ለጋሾቹ መካከል አንዱ የሆነው አሸናፊ አዲሱ።

ደማቸውን የለገሱት ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው በህክምና ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑ ተገልጾ በራሳቸው ተነሳሽነት ያደረጉት መሆኑም ተጠቅሷል።

ይህ ደም የመስጠት ተግባር የተጀመረው በአምስት ሰዎች መሆኑ ተገልጾ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ ደም የለገሱት ሰዎች ቁጥር 50 ደርሷል ተብሏል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በርካታ ደቡበ ኮርያዎች በርካታ የቅድመ ጥንቃቄና የምርመራ ስራዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እየሰሩ ነው ፤ ይህም ለሌሎች አገራት ምሳሌ ነው ብለዋል ደም የለገሱት ኢትዮጵያዊያን።

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮርያ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1963 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top