Connect with us

እነበረከት ስምኦን ፍርድ ቤት ቀረቡ

እነበረከት ስምኦን ፍርድ ቤት ቀረቡ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

እነበረከት ስምኦን ፍርድ ቤት ቀረቡ

በመዝገቡ አቶ በረከት ስምኦን አንደኛ ተከሳሽ ሲሆኑ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ዳንኤል ግዛው ሁለተኛና ሦስተኛ ተከሳሽ ሆነው ቀርበዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዛሬው ቀጠሮ በአንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች የሰነድ ማስረጃ ላይ የአቃቤ ሕግን አስተያየት ለመቀበልና ተጨማሪ የሰነድ እንዲያያይዝላቸው ለማድረግ እንዲሁም ሦስተኛ ተከሳሽ አሉኝ ያሉት ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያያይዝላቸው በጠየቁት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር።

ችሎቱ በአንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ላይ አቃቤ ሕግ አስተያየቱን በጽሁፍ ያቀረበ ሲሆን፣ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ እና የኢንደስትሪ ፓርኮችም እንዲያቀርቡ የተጠየቁትን የሰነድ ማስረጃ አቅርበዋል።
ሦስተኛ ተከሳሽ ይያያዝልኝ ያሉትን ማስረጃም ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል።

በተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ሌላ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል አቃቤ ህግ የጠየቀ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው የተጠየቀው ጊዜ ተከሳሾችን የሚያንገላታ በመሆኑ ከመዝጊያ ንግግር ጋር በጋራ ይቅረብ ሲሉ ጠይቀዋል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የመዝጊያ ንግግር የሚቀርበው ክርክር ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን በመጥቀስ አቃቤ ሕግ ቀድም ብሎ አስተያየቱን ይስጥ ብሏል።
በዚህም መሰረት አርብ መጋቢት 04/2012 ዓ.ም አስተያየት እንዲሰጥ ተብሏል።

ተከሳሾች ከህመምና አፋጣኝ ውሳኔ ከማግኘት አንፃር አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ካለበት ተደራራቢ ሥራና በተዘዋዋሪ ችሎት ምክንያት አጭር የሚባለውን ቀጠሮ መስጠቱን አስታውቋል።

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሠ ካሣ የጥረት ኮርፖሬሽንን በቦርድ ሰብሳቢነትና በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሲመሩ “ሥራን በማያመች ሁኔታ በመምራት የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል” በሚል ጥር 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው።(ቢቢሲ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top