Connect with us

እነበረከት ስምኦን ጥፋተኛ ተባሉ

እነበረከት ስምኦን ጥፋተኛ ተባሉ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

እነበረከት ስምኦን ጥፋተኛ ተባሉ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ ላይ በተከሰሱበት ወንጀል የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ።

በእነ አቶ በረከት ስምዖን የክስ መዝገብ የተከሰሱት አንደኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምዖን፣
ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ እና ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ግዛው በዐቃቤ ሕግ በቀረቡባቸው አራት ክሶች ሲከራከሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

ተከሳሾች ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በነበሩ የሥራ ውሎች የጥረት ኮርፖሬትን ጥቅም በሚጎዳ መንገድ ተንቀሳቅሰዋል የሚሉ አራት ክሶች ቀርበውባቸዋል።

ሁሉም ተከሳሾች ድርጊቱን አልፈጸምንም፤ ጥፋተኛም አይደለንም ሲሉ ክደው መከራከራቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ባዋለው ችሎት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።

በዚህም አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ ጥፋተኛ ሲባሉ ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ግዛው ከቀረቡት ክሶች ነፃ ናቸው ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየት ለማዳመጥ ለሚያዝያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ኢብኮ ዘግቧል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top