Connect with us

የአማራ ክልል ፖሊስ ነገ በኢዜማ ለቀረበበት ክስ መልስ ይሠጣል ተብሎ ይጠበቃል

የአማራ ክልል ፖሊስ ነገ በኢዜማ ለቀረበበት ክስ መልስ ይሠጣል ተብሎ ይጠበቃል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የአማራ ክልል ፖሊስ ነገ በኢዜማ ለቀረበበት ክስ መልስ ይሠጣል ተብሎ ይጠበቃል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ #ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀረበበትን ቅሬታ በሚመለከት በአካል ቀርቦ እንዲያስረዳ ጠየቀ።

ቦርዱ የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ ላይ ኢዜማ በተለያየ ጊዜ በጎንደር እና በደብረ ብርሃን ከተሞች ያዘጋጃቸው ሕዝባዊ ስብሰባዎች በአግባቡ ማካሄድ አለመቻሉን ፓርቲው አቤቱታ ማቅረቡን ጠቅሷል፡፡

በሁለቱም ከተሞች ላይም ሕዝባዊ ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ ፓርቲው የተደራጁ ኃይሎች ሲል የጠራቸው ቡድኖች የፈጠሩት ችግር የከተማው የፀጥታ ኃይሎች ከመከላከል ይልቅ ከችግር ፈጣሪዎቹ ጎን በመቆም ሕዝባዊ ስብሰባዎቹ እንዳይካሄድ እንቅፋት እንደሆኑበት ለቦርዱ በላከው አቤቱታ ላይ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች ምቹ ሁኔታን የመፍጠር እና የማገዝ ግዴታ እንዳለበት ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን በላከው ደብዳቤ ላይ ጠቅሶ ኢዜማ ያቀረበውን አቤቱታ በሚመለከት ፖሊስ ኮሚሽኑ ጉዳዩን ሊያስረዱ ከሚችሉ ኃላፊዎች እና ሰነዶች ጋር የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በመቅረብ እንዲያስረዳ ጠይቋል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top