Connect with us

ኢዜማ ገዥውን ፓርቲ ከሰሰ

ኢዜማ ገዥውን ፓርቲ ከሰሰ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ኢዜማ ገዥውን ፓርቲ ከሰሰ

ብልጽግና ፓርቲ የህዝብና የመንግስት ሃብትን ለምርጫ ቅስቀሳ እየተጠቀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ አስታወቀ።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ እና በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ ድርጊት ሌሎች ፓርቲዎችን ወደ አላስፈላጊ መንገድ የሚመራና አካሄዱ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ግንባታ የሚጎዳ በመሆኑ ፓርቲው ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ አሳስበዋል። ምርጫ ቦርድም ይሄንን ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲያስቆም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጠይቀዋል።

አያይዘውም የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነቶችን የሚያደበላልቁ እርምጃዎችን ማየታችን እጅግ አሳሳቢ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የፓርቲ ሳይሆኑ የመንግሥት ኃላፊነት ያለባቸው ተቋማት ለብልጽግና ፓርቲ ገንዘብ እንዲያዋጡ ማህበረሰቡ ላይ ጫና እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም የወረዳ ኃላፊዎች የባንኮችና የኢንሹራንስ ተቋማት አመራሮችን በግልፅ ገንዘብ እንዲያዋጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ ጠቁመው ይህ አካሄድ በፍጹም ለተጀመረውና ለሚታሰበው ዲሞክራሲ ምንም አይጠቅምም ሲሉም ተናግረዋል።

እነዚህ የመንግሥት ባለሟሎች ይህ ድርጊታቸው “ስህተት መሆኑን” እንኳን የሚረዱ አለመሆናቸውን የተናገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በመንግሥትና በፓርቲ መካከል ያለውን ቀይ መስመር መለየት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top