Connect with us

ቦርዱ በምርጫ ለሚሳተፉ አዲስ ፓርቲዎች ምዝገባ የ10 ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ

ቦርዱ በምርጫ ለሚሳተፉ አዲስ ፓርቲዎች ምዝገባ የ10 ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ቦርዱ በምርጫ ለሚሳተፉ አዲስ ፓርቲዎች ምዝገባ የ10 ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ክትልልና ምዝገባ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ተግባራት መካከል አዲስ ምስረታ ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማገዝ፣ የምዝገባ ሂደቱ ህጉ በሚጠይቀው መሰረት መከናወኑን ማረጋገጥ እና ድጋፍ መስጠት አንዱ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በቀድሞው ህግ መሰረት ተመዝግበው የሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እንዲያጠናቅቁ እያንዳንዱን ፓርቲ ሰነድ በመገምገም ዝርዝር ድጋፍ መስጠት እና መሟላቱን ማረጋገጥ ሌላው ነው፡፡

ቦርዱ እነዚህን ተግባራት አከናውኖ ለመጪው ምርጫ ፓርቲዎችን ብቁ የማድረጉ ስራ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ለመመዝገብና ለምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግለሰቦች ስብስቦች እንዲሁም ግንባርና/ቅንጅት መፍጠር የሚፈልጉ ፓርቲዎች፣ አስፈላጊ ሰነዶቻችሁን እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ እንድታስገቡ እናሳውቃለን፡፡

ከየካቲት 30 በኃላ የሚመጡ የምዝገባ ማመልከቻዎች በተለመደው አግባብ የሚስተናገዱ ቢሆንም ያለው የአሰራር ሂደት ከሚወስደው ጊዜ አንጻር መጪው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እንገልጻለን ብሏል ቦርዱ።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top