Connect with us

ምርጫው ቅርጫ እንዳይሆን!

ምርጫው ቅርጫ እንዳይሆን!
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ምርጫው ቅርጫ እንዳይሆን!

ምርጫው ቅርጫ እንዳይሆን!
(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ሰሞኑን ደምቆ እንደምንመለከተው ለዶ/ር አብይና የብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች (ትግራይን አይጨምርም) የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ነው፤ ይህ ለውጡን በስሜት ለምንደግፍ ዜጎች አስደሳች ነው፤ ድጋፋችን ተጠየቃዊ ከሆነ ግን ያስፈራል፡፡

የሚያስፈራው የብልጽግና ፓርቲ ተቀባይነት ማግኘት አይደለም፤ በእነዚህ ቦታዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ማድረግ እንኳን መቸገራቸው ነው፡፡

እኔ የብልጽግና ፓርቲ (የለውጡ) ደጋፊ ነኝ፤ ሰፊ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ በምርጫ እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ፡፡ ብቻውን ጋልቦ እንዲቀድም፣ ብቻውን ተወዳድሮ እንዲመረጥ ግን አልፈልግም፤ አልፈቅድምም፡፡ ይህ ስቃወመው የኖርኩት የዴሞክራሲ ሾተላይ ነውና አሁንም ልደግፈው አልችልም፡፡

ዜግነትን መሰረት አድርገው የተደራጁ ፓርቲዎች ብሄርን መሰረት አድርገው በተደራጁ ፓርቲዎች ክልል ቢሮ መክፈት፣ ስብሰባ ጠርቶ ዜጎችን ማወያየት አልቻሉም፡፡ በኦሮምያም ቢሆን መሰብሰብና መሰለፍ የውሀ መንገድ እየሆነ ያለው ለብልጽግና ነው፡፡

ይህ በዚሁ ከቀጠለ መጪው ምርጫ በየክልሉና ዞኑ አብላጫ ቁጥር ያላቸውን ብሄረሰቦች የሚወክሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሀገሪቱን በምርጫ ስም የሚቃረጡበት እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ከምርጫው የሚጠበቀውን ሰላምና ዲሞክራሲም አያመጣም፡፡ በመሆኑም ፓርቲዎች በመላው ሀገሪቱ ተንቀሳቅሰው፣ ዜጎችን የማወያየትና ፕሮግራማቸውን የማስተዋወቅ ፖለቲካዊ መብታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ምርጫን ማካሄድ ትርጉም አይኖረውም፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top