Connect with us

የኮሮና ቫይረስ እና ቱሪዝም

የኮሮና ቫይረስ እና ቱሪዝም
Photo: Associated Press

ኢኮኖሚ

የኮሮና ቫይረስ እና ቱሪዝም

የኮሮና ቫይረስ እና ቱሪዝም | በአስራት በጋሻው

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ቢመጣም አብዛኛውን ተጠቂ የሆኑት የኤሽያ ሀገራት ናቸው። ይሁን እንጂ በሽታው በቱሪዝም ላይ ያደረሰው አደጋ አለምአቀፋዊ ነው።

የኒው ዬርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ፖትሪክ ፖት እንደጻፈው በየእለቱ በቱሪስት የምትጨናነቀው የጃፓን ኩዬቶ አሪሻያማ የቀርከሃ ደን ቀርከሃውን ከሚያዛውዘው ንፋስ በስተቀር የሰው ድምጽ አይሰማባትም ።

በሆንክ ኮንግ በየእለቱ ወደላንቱ ደሴት ቱሪስት የሚያጓጉዘው ኬብል ካር በአየር ላይ ብቻውን ይወዛወዛል።
የቬትናም ላንተርን ድልድይ ላይ ዝር የሚል ቱሪስት የለም።

በካምቦዲያ የቱሪስት ሎጆች ላለፋት ሶስት ሳምንታት ምዝገባ አልተቀበሉም።

በአለም አቀፋ የቱሪዝም ካውንስል መረጃ እ ኤ አ በ2018 ቱሪዝም ለአለም ኢኮኖሚ ከ8 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝቷል ።
የኮርና ቫይረስ የአለም ኢኮኖሚ ወደ ኃላ ይጎትታል።አየር መንገዶች ብቻ የ29በሊዬን ዶላር
ገቢ ያጣሉ።

ለቫይረሱ የቀረቡት የቻይና አጎራባች አገሮች ብቻ ሳይሆኑ የአውሮፖ ሀገራትም ችግሩ ነካክቶአቸዋል። ጣልያን ከ300 በሽተኞች ተመዝግበው በሎምባርዲ ግዛት የሚያገናኙ 10 የሚጎበኙ ከተሞችን ዘግታለች። ቪንቼም የካርኒቫል ቀጠሮዋን አቋርጣለች።

የደቡብ ኤሽያ ሀገራት ከቻይና ይመጣሉ ተብለው ለሚጠበቁ ታሳቢ ተደርገው የተሰሩ አዳዲስ ሎጆች እና ሆቴሎች አሁንም ሆነ ለወደፊት የጉብኝት ፕሮግራሞች ለመስተንግዶ ቦታ አልተያዘላቸውም። አየር መንገዶች ከምእራቡ አለም የሚነሱ መንገደኞች አላመጡላቸውም ።

አዳዲስ የመዝናኛ እና የመቆመሪያ ቤቶች ኦና ሆነዋል።

ከቻይና የሚነሱ ቱሪስቶች መጥፋት የጎዳቸው እንደ ታይላንድ ቬትናም ካምቦዲያ ሲንጋፖር እና ማሌዝያ ከ3ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያጣሉ።ወደነዚህ ሀገራት የሚደረገው የአየር በረራም  20 በመቶ ቅናሽ አሳይቶአል። ኦንደ ፖት ጽሁፍ ከሆነ የቱሪዝም ገቢ እያሽቆለቆለ የሚታየው በአለማቀፍ ደረጃ ነው።

አሜርካውያን ከሀገራው ውጭ ያሉ ጉዞአቸውን ሰርዘዋል ።

በፈረንጆች 2018 150 ሚሊዬን ቻይናውያን ቱሪስቶች 277ቢሊዮን ዶላር ለአለም ኢኮኖሚ በቱሪዝም አበርክተዋል።
ዛሬ ላይ ቻይና በቫይረሱ ጉዳቱ በርትቶባታት ስታቃስት የአለፈው አመት ዘገምተኛ የኢኮኖሚ እድገት እና የባላንጣዋ አሜሪካ የንግድ ውድድር እሰጥ አገባ ደቁሶአት አልፏል ብሎ ምህረት አላደረገላትም።

ወደ አሜሪካ ለማምራት ያሰቡ ከጃፓን እና ከደቡብ ኮርያ የሚነሱ ሀገር ጎብኚዎች አትድረሱብን ተብለዋል ።በቂ ምክንያት ከሌላቸው ጉዞአቸውን እንዲያዘገዩ ተመክረዋል።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top