Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመድሃኒት ቁሳቀሶችን በማጓጓዝ ቻይናን እየረዳ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመድሃኒት ቁሳቀሶችን በማጓጓዝ ቻይናን እየረዳ ነው
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመድሃኒት ቁሳቀሶችን በማጓጓዝ ቻይናን እየረዳ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቻይና መንግሥት ኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶች እና መድሃኒቶች ከተለያዩ ዓለማት ወደቻይና እያጓጓዘ መሆኑ ተሰማ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደቻይና የሚያደርገውን በረራ አጠናክሮ በመቀጠል የኮሮና ቫይረስን ክፉኛ የጎዳትን ቻይና ለመታደግ ከተለያዩ አገራት የተገኙ ድጋፎችን ወደቻይና ከተሞች በማጓጓዝ የሰብዓዊ ተግባር ሥራውን እያከናወነ መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘ መረጃ ጠቁሟል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ እንደብሪቲሽ አየር መንገድ ያሉ ትላልቅ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ወደቻይና የሚያደርጉትን በረራቸውን ሲያቋርጡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን በመከላከል ላይ ያተኮረ ስትራቴጂ ከመንግሥት ጋር በመንደፍ ሲከላከል ቆይቷል፡፡

 

በተያያ ዜና በዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት እስከ የካቲት 15/2012 ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሶስት (77 ሺ 923) ሲሆን ሁለት ሺህ ሶሶት መቶ ስልሳ አንድ (2 ሺ 361) ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአጠቃላይ ከጥር 15 ቀን 2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች 178 ሺ 487 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4 ሺ 509 በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች 305 ሺ 497 በሙቀት መለያው አልፈዋል፡፡

ከየካቲት 13 – 14/2012 ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች 11 ሺ 394 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 256 በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ 11 ሺ 650 በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች በሙቀት መለያው አልፈዋል፡፡

እንዲሁም ከየካቲት 13 – 14/2012 በክትትል ላይ የነበሩ ነገር ግን 14 ቀናት የሞላቸው 178 ሰዎች ክትትላቸው የጨረሱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 884 የሚሆኑት ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ሲሆኑ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ያለበት ሰው አለመኖሩን ኢንስቲትዩቱ ያረጋግጣል፡፡

ከየካቲት 12 ቀን 2012 ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ 3 አዳዲስ ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) የደረሱ ሲሆን በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጎ የበሽታውን ምልክት ያላሳዩ መሆኑ ተረጋግጧል፡:

በአጠቃላይ ከጥር 15 ቀነ 2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 68 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

ከነዚህም ጥቆማዎች 18ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስላላቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም 18 ቱንም የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top