Connect with us

አብን ሊቀመንበሩን አነሳ፣ የሕግ እስረኛውን ክርስቲያን ታደለ ወደተሻለ ኃላፊነት አሸጋገረ

አብን ሊቀመንበሩን አነሳ፣ የሕግ እስረኛውን ክርስቲያን ታደለ ወደተሻለ ኃላፊነት አሸጋገረ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

አብን ሊቀመንበሩን አነሳ፣ የሕግ እስረኛውን ክርስቲያን ታደለ ወደተሻለ ኃላፊነት አሸጋገረ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን የምርጫ ቦርድ ታዛቢ በተገኘበት በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል።

ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አብን የአማራን ሕዝብ ጥያቄ መመለሥ በሚያስችለውና ወቅቱ በሚፈልገው ልክ ይገኝ ዘንድ ላለፉት ጊዜያት የመጣበትን መንገድ መርምሮ በጥናት ላይ የተመሰረተ መዋቅራዊ ማሻሽያ መዘጋጀቱን ገለፀው በዚህ ላይ ጠቅላላ ጉባዔው በደንብ ተወያይቶ አቋም እንዲይዝበት ጠይቀዋል።

ጉባዔው በመጀመረያ ቀን ውሎው የአብን መዋቅራዊ ማሻሽያ(ሪፎርም) አስፈላጊነትና አላማ፣ የንቅናቄው ጥቅል የሥራ ክንውን ሪፖርት፣ የፋይናንስ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ሪፖርት፣ የብሔራዊ ም/ቤቱ ሪፖርት፣ የተሻሻለው የንቅናቄው መተዳደሪያ ደንብና ቀርቦ በጠቅላላ ጉባዔው አባላት ሰፊ ውይይት ካደረገ በኃላ አፅድቋል።

ጠቅላላ ጉባዔው 5 ተለዋጭ አባላት ያሉት 45 የንቅናቄውን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥም መርጦ ያፀደቀ ሲሆን የተመረጡት አባላትም የድርጅቱን ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር መርጠዋል። በተጨማሪም በሊቀመንበሩ የቀረቡለትን ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚዎችን አፅድቋል። በዚህም መሰረት 9ኙ የአብን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች፦

1. አቶ በለጠ ሞላ – ሊቀመንበር

2. አቶ የሱፍ ኢብራሂም – ም/ሊቀመንበር

3. አቶ አዲስ ኃረገወይን- የፖሊሲ ስትራቴጂ ኃላፊ

4. አቶ ጣሂር ሞሐመድ- የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

5. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም- የውጭ ጉዳይና ዓለማቀፍ ግንኙነት

6. አቶ ጋሻው መርሻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ

7. አቶ መልካሙ ፀጋዬ- የፅሕፈት ቤት ኃላፊ

8. አቶ ጥበበ ሰይፈ- የሕግና ስነምግባር ኃላፊ

9. አቶ ክርስቲያን ታደለ- የፓለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው።

በተያያዘ ዜና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ ማክሰኞ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ 4 ኪሎ ግንፍሌ ድልድይ አጠገብ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ከወቅታዊ የፓርቲውና አገራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top