Connect with us

ዘረኝነት ክፉ ነው መቆሚያ የለውም ወንድምህ ላይ ቦንብ ያስወረውርሃል

ዘረኝነት ክፉ ነው መቆሚያ የለውም ወንድምህ ላይ ቦንብ ያስወረውርሃል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ዘረኝነት ክፉ ነው መቆሚያ የለውም ወንድምህ ላይ ቦንብ ያስወረውርሃል

ዘረኝነት ክፉ ነው መቆሚያ የለውም ወንድምህ ላይ ቦንብ ያስወረውርሃል፤ ከሚሰጋ ተቃዋሚ ወደሚያሰጋ ተሸጋግረናል፡፡ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ ቦንብ የሚጣልባት ሀገር፡፡
****
ከስናፍቅሽ አዲስ

ዘረኝነት የእከሌ የእከሌ የለውም እነ እከሌን ለማጥቃት የጀመረው ልምምድ ውሎ አድሮ እንደ ድመት የራስን ልጅ የሚያስበላ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ የትኛውም ወገን ዘረኛ ከሆነ መጨረሻው እንዲህ የራሱን ወገን የመብላት ምኞት ማሳደር ነው፡፡

በኦሮሚያ እየሆነ ያለው ነገር ያሳስባል፡፡ ክልሉን እንደ ራሳቸው ላፕ ቶፕ የግል ንብረታቸው ያደረጉ ዘረኞች ውለው አድረው ዜጎች የመረጡትን የመደገፍ መብት እንደማይፈቀድላቸው እያሳዩን ነው፡፡

በኦሮሚያ ብልጽግናን ከጎንህ ነን የሚሉ ሰልፎች ነገን ማየት የቻሉ ዜጎች የፈጠሩት አብዮት ነው፡፡ የአክራሪዎች ባቡር መድረሻው የት እንደሆነ ያወቁ ዜጎች ከተሳፈሩበት ወርደዋል፡፡ ማህበራዊ ህይወትን በሚፈትነው፣ አብሮ መኖርን በሚያሳድደው፣ ሁሉን በቋንቋና በጎሳ በሚወጥነው አልፎም ለሃይማኖት አንድነት ጭምር ሳንካ ከሆነው የጭፍን ድጋፍ ባቡር እየወረዱ ነው፡፡

ማንም ሰው የተሻለች ሀገር ይፈልጋል፡፡ የተሻለ ሀገር ፍለጋ ቋንቋው ወደማይከበርበት እሴቱ ወደማይታወቅበት በብሔሩ ወደማይወከልበት ዓለም የሚሰደደው የተሻለ ነገር ፍለጋ ነው፡፡ ከሁሉም የሚሻለው ብሔርህ ነው የሚሉ አንቂዎች ቢያንስ ልጆቻቸውን የተሻለች ሀገር ዜጋ አድርገዋል፡፡ የራሳቸውን ፓስፖርት ቀይረዋል፡፡ ሀገራቸው ወገኔ ያሉት ግን እንዲቀየር አይደለም ውሎ እንዲገባ አልፈቀዱለትም፡፡

በቅርቡ የአትሌት ሌሊሳን ቃለ መጠይቅ ሰማሁ፤ እንዲህ የትግል ውጤቱ እርስ በእርስ መባላት መሆኑን ባውቅ ያኔ ባልተቃወምኩ ዓይነት ንግግር አደረገ፤ ይህ ዘመን የአትሌቱን ልብ ሰብሮት ነው፡፡ ይህ ዘመን ለምን እንዲህ ሆነ የሚሉ ሰዎች ከመጠየቅ አልፈው ከዚህ በኋላ መከራው እንዳይቀጥል በቃ ብለዋል፡፡ በቃ ሲሉ ግን ሞት እየተፈረደባቸው ነው፡፡

አሸባሪ በሌላው ወገን ላይ መጨከን ፈልጎ እንዲህ ያለ ነገር ፈጸመ ሲባል እንሰማለን፤ የእኛው ግን ይለያል በክረምት ምረጠኝ የሚለው ሰው ላይ በበጋ ቦንብ መጣል ነው፡፡ ምሳ እየበላ የፖሊስ መሪ የሚገደልበት ትግል ከድመት የከፋ የራስን ልጅ መብላት ነው፡፡

በሀገራችን ፖለቲካ የምናውቀው ተቃዋሚ ሲሰጋ ነው፡፡ ተቀዋሚ ምን ይገጥመኝ ይሆን ሲል ነው፤ ይገድሉኛል ብሎ ሲሰደድ ነው፡፡ አሁን ተቃራኒ ነው፡፡ ተቃዋሚው እንዳይገድል መንግስት ይሰጋ ጀምሯል፡፡ ተቃዋሚም ከመስጋት ወደ ማስጋት ተሸጋግሯል፡፡

በዓለም ታሪክ ጠመንጃ በእጁ የያዘን መንግስት የሚደግፉ ደጋፊዎች በተቃዋሚዎች ቦንብ የሚጠቁባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ትመስለኛለች፡፡ ግን አያዋጣንም፤ ከጥፋት መንገድ ካልተመለስን ኪሳራው የሁላችንም ነው፡፡ በፈንጂ ድምጽ የተሰራች ሀገር የበለጸገ ፖለቲካ ያሸነፈ ፍቅር የለምና፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top