Connect with us

በአምቦ የቦምብ ጥቃት ያደረሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በአምቦ የቦምብ ጥቃት ያደረሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ህግና ስርዓት

በአምቦ የቦምብ ጥቃት ያደረሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ትናንት በአምቦ ከተማ ለዶክተር አብይ አህመድና ለለውጥ አመራሩ የድጋፍ ሰልፍ ሲካሄድ የቦምብ ጥቃት ያደረሱ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ዲሪሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ወደ አምቦ እየገቡ በነበሩ ፈረሰኞች ሲሆን፤ከ10 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ተጎጅዎች በአምቦ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡

ጥቃት ያደረሱት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጹት ከንቲባው፣ ጉዳዩን ፖሊስ በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን መግለጫ እንደሚሰጥበት አስታውቀዋል።

የከተማዋ አስተዳደርም ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ምንም እንኳን ይህ አደጋ ቢያጋጥም የድጋፍ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አመልክተዋል፡፡

ምንጭ:- ኢ.ፕ.ድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top