Connect with us

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኮትዲቯሩን የባህላዊ ንጉስ አነጋገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኮትዲቯሩን የባህላዊ ንጉስ አነጋገሩ

ባህልና ታሪክ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኮትዲቯሩን የባህላዊ ንጉስ አነጋገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ትናንት ኮትዲቯራዊውን የባህላዊ ንጉስ ቸፊዜይ ጃን ጌርቫስን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በአፍሪካ አገር በቀል የባህላዊ አስተዳደር መሪዎች ሚናን በሚመለከት ውይይት አድርገዋል።

አቶ ገዱ በዚህ ወቅት እንደገለጹት አፍሪካውያን ጠቃሚ የሆኑ ባህላዊ የግጭት አፈታትን ለዘመናት ያዳበሩ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ባለቤት መሆኗን በማስታወስ፣ በአሁኑ ወቅትም ግጭቶች በሚፈጠሩበት ወቅት በባህላዊ መንገድ እንዲፈቱ በማድረግ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ እንደሆነ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሸህዎችን ለግጭት አፈታት በሰፊው የመጠቀም ልምድና ባህል ያላት ሀገር እንደሆነች ያነሱት አቶ ገዱ፤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ከሌሎች አፍሪካዊያን አቻወቻቸው ጋር በጋራ እንዲሰሩ መንግስት አስፈላገውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

ንጉስ ቸፊዜይ ጃን ጌርቫስ በበኩላቸው ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቅር እንዳላቸውና አፍሪካውያን የሆኑ በርካታ ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችን ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በማቀራረብ በሰላምና ልማት ዙሪያ በጋራ እንዲሰሩ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ይህንኑ ሃሳባቸውን ወደተግባር ለመቀየር በአዲስ አበባ ፅ/ቤት ለመክፈት እቅድ እንዳላቸው በመግለፅ የኢትዮጵያን መንግስት ድጋፍ እንደሚፈልጉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። #EBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top