Connect with us

በዩኒቨርሲቲዎች በ2ኛው ሴሚስተር የታሪክ ትምህርት መስጠት እንደሚጀመር ተገለጸ

በዩኒቨርሲቲዎች በ2ኛው ሴሚስተር የታሪክ ትምህርት መስጠት እንደሚጀመር ተገለጸ
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

በዩኒቨርሲቲዎች በ2ኛው ሴሚስተር የታሪክ ትምህርት መስጠት እንደሚጀመር ተገለጸ

በትምህርት ፍኖተ ካርታው ምክረ ሐሳብ መነሻነት ለዩኒቨርሲቲ ጀማሪ ተማሪዎች 2ኛው ሴሚስተር የታሪክ ትምህርት ማስተማር እንደሚጀመር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለታሪክ ትምህርት ማስተማሪያነት የተዘጋጀው ሞጁል የተለያዩ የዘርፉ ምሁራንን አስተያየቶች አካትቶ ለማስተማሪያነት ዝግጁ ሆነ

በወርክሾፑ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የታሪክ ትምህርት ከቀደመው ህዝብ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነልቦናዊ ገፅታዎችን በመረዳት ከቀደመው ትውልድ ከስኬቱም ከውድቀቱም፣ ከድሉም ከሽንፈቱም፣ ከጥንካሬውም ከድክመቱም፣ ከመልካሙም ከመጥፎውም፣ ለዛሬ ህላዊ ለነገም ትልም ጠቃሚ ትምህርት የሚወሰድበት ሲሆን ይህም በራስ መተማመን የመንፈስ ጥንካሬና ኩራት ይሰጣል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣የታሪክ ተመራማሪዎችና ምሁራን በተገኙበት በኢትዮጵያና አፍሪካ ቀንድ ታሪክ ማስተማሪያ ሞጁልን አስመልክቶ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል በተካሄደ የአስተውሎት መድረክ ላይ እንደገለጹት፤ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ ለአንደኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጋራ ትምህርቶች( ኮመን ኮርሶች) መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተመላክቷል፡፡በዚህ መሰረት የታሪክ ትምህርትን ጨምሮ 15 የትምህርት ዓይነቶች ተዘጋጅተዋል።

በ2012 ዓ.ም አዲስ ገቢ ለሆኑ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተዘጋጁትን አዳዲስ የትምህርት አይነቶች(ኮርሶች) መሰጠት ቢጀምሩም የታሪክ በማስተማሪያ ሞጁል ባለመድረሱ ሊሰጥ ባለመቻሉ 2ኛ ሴሚስተር መስጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡

ከትምህርት ስርዓቱ ስብዕና ያለው ትውልድ ማፍራት ካልቻለ ኢንቨስትመንቱ እንደከሰረ እንደሚቆጠር የገለጹት ፕሮፊሰር ሂሩት፣ባለፉት ዓመታት የትምህርት ስርዓቱ ምን ጉድለት አለበት?፣ እንዴት ይስተካከል? እና ምን ይጨመር? በሚል በትምህርት ፍኖታ ካርታው ተካትቶ ሰፊ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ፕሮፌሰሯ እንዳሉት፤ በሁለተኛው ሴሚስተር የሚጀመረው የታሪክ ትምህርት(ኮርስ) አስፈላጊነት የሚያከራክርና የሚያሻማ አይደለም።ምክንያቱም ትውልዱ ያለፈውንና የቀደመውን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ፣ስነልቦናዊ እና ሁሉንም ሁለንተናዊ ገጽታዎች ማወቅ አለበት። ከውድቀቱ፣ከስኬቱና ከሽንፈቱም በጎ በጎውን መማር ይኖርበታል፡፡

“እንኳን ኢትዮጵያን ያህል ታላቅ አገር ትናንት የተፈጠሩትም አገራት የራሳቸው ታሪክ እንዳላቸው ያስታወሱት ሚኒስትሯ፣ እጥረቱ ምሁራኖች ያሉትን የታሪክ አከራካሪ ጉዳዮች በጥናትና ምርምር በማድረግ አጣርተው መፍትሄ ማበጀት አለመቻላቸው እንደሆነ አስገንዝበዋል።

“በሚጠቅመን የጋራ ታሪክ ላይ አትኩረን 18 ዓመት ዕድሜ ለሞላው ወጣት የሚመጥንና በአቅሙ ተዘጋጅቶ እንዲማር መደረጉ ስለአገሩ መረጃና እውቀት ይዞ እንዲወጣ ያግዘዋል “ብለዋል፡፡

የታሪክ ሰነዱን ካዘጋጁት መካከል አንዱ የሆኑት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህሩና ተመራማሪው አቶ ካሱ ቱሚሶ በበኩላቸው፤በሞጁሉ ዝግጅት ሂደት ፈታኝ ነገሮች ቢያጋጥሙም ወደ መልካም እድል ተቀይረው ሂደቱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ማስቻሉን አብራርተዋል።

የታሪክ ማስተማሪያ ሞጁል ረዥም የዝግጅት ሂደት ማለፉን ያነሱት አቶ ካሱ በባለሙያዎቹ የተዘጋጀው በስድስት ምዕራፎች ተገምግሞና ግብዓት ተጨምሮበት የተጠናቀቀውና ስምምነት ላይ የተደረሰበት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት መላካቸውን አስረድተዋል።

የታሪክ የዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ማስተማሪያ ሞጁል በ187 ገጽ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ርዕሰ ጉዳዮች በየደረጃው በተከናወኑት የዝግጅት፣የክርክርና የውይይት ሂደት መግባባቶች የተፈጠረባቸው መሆኑን ገልጸዋል።ነገር ግን የአኖሌ ጉዳይ በሌሎች ጥናቶች መደገፍ እንደሚገባ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምክረ ሐሳብ እንደሰጠበት አስገንዝበዋል፡፡

አዲስ ዘመን የካቲት 13/2012

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top