Connect with us

የብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሐውልት በተወለዱባት ከተማ ሊቆም ነው

የብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሐውልት በተወለዱባት ከተማ ሊቆም ነው

ባህልና ታሪክ

የብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሐውልት በተወለዱባት ከተማ ሊቆም ነው

የብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሐውልት በተወለዱባት ከተማ ሊቆም ነው፡፡
የሐውልቱ ሙሉ ወጪ በአንድ አሜሪካን ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ይሸፈናል፡፡
****
በኢትዮጵያ የረዥም ዘመን ታሪክ በሴት ነገሥታት በኩል ስማቸው ጎልቶ ከሚነሳው አንዷ የሆኑት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ይባላሉ፡፡

በእርግጥም ጣይቱ የኢትዮጵያ ብርሃን ነበሩ፡፡ ዘመን የማይሽረው የአድዋ ድል ሲነሳ ታላቋ ሴት ስማቸው አብሮ ከፍ የሚል የጥቁር ሁሉ ኩራት ናቸው፡፡ የዛሬይቷ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባም የተመሰረተችውና ስሟን ያገኘችው በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ነበር፡፡

ጣይቱ ብጡል ለስማቸው መታሰቢያ በሀገራቸው በኢትዮጵያ አንዳችም የመታሰቢያ ሐውልት ሳይቆምላቸው ኖሯል፡፡ ይሄንን የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን በትውልድ ከተማቸው በደብረ ታቦር የእቴጌይቱን ሐውልት ለማቆም ወስነዋል፡፡

ትናንት የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በደብረ ታቦር ከተማ የመሠረተ ድንጋዮ የተቀመጠው የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የመታሰቢያ ሐውልት ሙሉ ወጪም በአሜሪካን ሀገር በሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚሸፈን ይሆናል ብለዋል አቶ ደህናሁን እምሩ ደስታ መሠረተ ድንጋዮ በተቀመጠበት ሥነ-ሥርዓት ላይ፤ የመሠረተ ድንጋዮን የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ እምቢያለ እና አቶ ደህናሁን እምሩ ደስታ ያስቀመጡ ሲሆን ሐውልቱ በቀጣዩ ዓመት በምናከብረው የአድዋ ድል በዓል ማለትም የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ተጠናቆ እንደሚመረቅ ለድሬ ቲዮብ ዘጋቢያችን አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top