Connect with us

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሃውልት ዛሬ ተመርቋል፡፡

በሃውልቱ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ የተለያዩ ድርጅቶ፣ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

ዛሬ ለምርቃት የበቃውን የኢንጅነር ስመኘው ሃውልት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው ያሠራው፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢንጅነር ስመኘው ባለቤት እናት ወይዘሮ መንበረ መኮንን እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሃውልቱን በማሠራቱና ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከጎናቸው በመሆን እያደረገ ያለውን ድጋፍ በመግለፅ አመሥግዋል፡፡

 

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር ነው›› ያሉት ወይዘሮ መንበረ ኢንጅነር ስመኘውንም ሕዝቡ በልቡ ሲያስታውሰው እንደሚኖርም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ደግሞ ለሀገር አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎች ቢሞቱም ሥራቸው ግን ታሪክ ሆኖ ሁልጊዜ ሲታወስ እንደሚኖር ገልፀዋል፡፡

‹‹የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲታወስ ሁልጊዜ ስመኘው ለምልሞ ይኖራል›› ያሉት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለሚመጣው ትውልድ ህያው ሆነው እንደሚኖሩም ተናግረዋል፡፡

 

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀበመታሰቢያ ሃውልቱ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶክተር፣ ኢንጅነር)፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶክተር፣ ኢንጅነር)፣ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሮማን ገብረሥላሴ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የኢንጅነር ስመኘዉ ቤተሰቦችና ወዳጆች ተገኝተዋል፡፡

የሃውልት ምርቃቱ ከኢትዮጵያ የሰማዕታት መታሰቢያ 83ኛ ዓመት ጋር በታላቅ ድምቀት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡

ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top