Connect with us

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት በዛሬው የጨፌ ስብሰባ ከተናገሩት

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት በዛሬው የጨፌ ስብሰባ ከተናገሩት
Photo: Facebook

ፓለቲካ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት በዛሬው የጨፌ ስብሰባ ከተናገሩት

– ከለውጡ በተቃራኒ የሚሠሩ ኃይሎች የጥፋት ዘመቻ በማካሄድ በክልሉ እና በመላው ሀገሪቱ ውስጥ የታየውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል ለማጨለም ሕዝቡን በሃይማኖት እና በብሔር የሚያጋጩ አጀንዳዎችን በመቅረፅ ለውጡን ለማደናቀፍ ሲንቀሳቀሱ ነበር፣

– በመላው ሀገሪቱ ብጥብጥ እንዲፈጠር እና በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸው እንዳይማሩ ሲያደርጉ ነበር፣

– “የነፃነት ታጋይ ነኝ” በሚል ራሳቸውን የሚጠሩ የ”ሽፍታ ኃይሎች” የገዳ አባቶች፣ የኦሮሞ ሕዝብ እና መንግሥት ያቀረቡላቸውን ጥሪ ችላ በማለት እና መንግሥት የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት ሲል ያሳየውን ትዕግሥት እንደ ፍርሃት በመቁጠር የጦር መሣሪያ ታጥቀው ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ውስጥ ነፍስ እና ንብረት እያጠፉ እንዲሁም በሕዝባችን ላይ የሥነ-ልቦና ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ፣

– እነዚህ ኃይሎች በአንድ ወገን ብጥብጥ በማስነሳት መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማስከበር እንዳልቻለ በማስመሰል በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማሰከበር የሚወስደውን እርምጃ በሕዝብ ላይ የተቃጣ ጥቃት በማስመሰል የተወሳሰበ ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ቆይተዋል፣

– አሁን ያለንበት ወቅት በሕዝባችን የየዕለት ኑሮ እና ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው በርካታ ትላልቅ ኹነቶች እየተመዘገቡበት ያለ ወቅት መሆኑን ተገንዝበን ሕዝባችን እና አመራሩ በከፈለው መስዋዕትነት በመላው ሀገራችን እና በክልላችን እየመጣ ያለው ለውጥ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ሁሉም ወገን ተሳትፎ ማድረግ እና የራሱን ሚና መጫወት ይገባዋል፣

(ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top