Connect with us

“ወንጀልን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"ወንጀልን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“ወንጀልን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ወንጀልን ከብሄር ጋር ማያያዝ እንደማይገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋር በተወያዩበት መድረክ አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ከዚህ ቀደም በተደረገ የኢህአዴግ የጥልቅ ተኃድሶ ግምገማ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሉና አብዛኞቹ የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸውን በማስታወስ ጉዳያቸው በእርቅ እና በይቅርታ እንዲታይ የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከዚህ ቀደም በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ወንጀለኝነትን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ማንኛውም ሰው በሰራው ወንጀል በህግ ይዳኛል ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል በመሰረተ ልማት እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች እየተገለለ ነው የሚል ስጋት መኖሩንም አመራሮቹ ለጠቅላይ ሚንስትሩ አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድም በምላሻቸው ለትግራይ ክልል በፌደሬሽን ምክር ቤት በወጣው ቀመር መሰረት የበጀት ክፍፍሉ ተጠቃሚ መሆኑን አስታውሰው ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለመንገድ፣ ለውሃ እና የመስኖ ስራ ለክልሉ የተመደበውን በጀት ሳይጨምር 8.2 ቢሊዮን ብር በጀት ለትግራይ መመደቡን ተናግረዋል፡፡

ክልሉ ከተለያዩ አካላት የፀጥታ ስጋት አለበት በሚል ለተነሳው ጥያቄም ጠቅላይ ሚንስትሩ የክልሉን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል አስተማማኝ ሀይል መኖሩን ለትግራይ ክልል የብልፅግና አመራሮች አረጋግጠውላቸዋል፡፡

አመራሮቹ በክልሉ ይታያሉ ባሏቸው ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ አንስተው ምላሽም ተሰጥቷቸዋል፡፡(ኢቢሲ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top