Connect with us

በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚሞክር ማንኛውም አካል ….

በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚሞክር ማንኛውም አካል በሩ ዝግ መሆኑን ማወቅ አለበት- የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚሞክር ማንኛውም አካል ….

በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚሞክር ማንኛውም አካል በሩ ዝግ መሆኑን ማወቅ አለበት- የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ

በመግደልና በጭካኔ ህዝቡን በማስፈራራት በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚሞክር ማንኛውም አካል በሩ ዝግ መሆኑን ማወቅ እንዳለበት የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡

አፈ ጉባኤዋ ይህንን ያሉት የጨፌ ኦሮሚያ 11ኛ መደበኛ ጉባኤ 5ተኛ ዓመት የስራ ዘመን በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው፡፡ ወይዘሮ ሎሚ እንዳሉትም ህዝቡን በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ለማሥገባት የአካባቢው ሰላም መረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡

መንግስትም ባለፉት ሁለት አመታት በምእራብና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ የተከሰተውን የሰላም ችግር ለመፍታት ያደረገው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ህዝቡን ከለላ በማድረግ አላማቸውን እውን ለማድረግ ተደብቀው የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎች የመንግስት የሰላም ስራ እንዲደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብለዋል አፈጉባኤዋ፡፡

ይህም የስልጣን ጥማታቸውን ለመወጣት የሚያደርጉት ጥረት በህዝብና በመንግስት ተሳትፎ መቼም እንደማይሳካ በማወቅ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጨፌ ኦሮሚያ ስም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችም በበኩላቸው ከህዝብና ከመንግስት ጎን በመቆም ለሰላምና መረጋጋት መስፈን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ወ/ሮ ሎሚ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

(ምንጭ:-ኢ.ፕ.ድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top